ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በአፋር ክልል አሸባሪው የህወሃት ቡድን በፈጸመው ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች የ100 ሚሊዮን ብር የገንዘብና ለተጎዱ ተቋማት ደግሞ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ።
ከገንዘቡ ሌላ ከተደረጉት ቁሳቁሶች መካከል “ፒክ አፕ ” እና የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ኮምፒውተሮችና ሌሎችም የቢሮ መገልገያዎች ይገኙበታል ተብሏል።
ድጋፉን የከተማ ልማትና መሠረተ-ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ አስረክበዋል።