ኢትዮጵያ ነገ ዜና | ሁለቱ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች መሰረተ ልማትን መጋራት፤ ኢንቱኮኔክቲቪቲ ማለትም የሁለቱ ደንበኞችን ማገናኘት አና ብሄራዊ ሮሚንግ ማለትም አንዳቸው የሌላኛቸውን ኔትዎርክ ለመጠቀም የሚያስችላቸውን ስምምነት ለማድረግ ከመስከረም ወር ጀምሮ ሲሰሩ የነበር ቢሆንም እስካሁን ንግግራቸውን ውጤታማ መሆን አልቻለም፡
በሁለቱም አገልግሎቶች ሰጪዎች እንደምክንያት ከተነሱት አንዱ የኪራይ ዋጋ ሲሆን የሳፋሪኮም ሀላፊዎች በኢትዮ ቴልኮም የቀረበው ዋጋ ውድ እንደሆነ ሲገልፁ የኢትዮ ቴልኮም ሃላፊዎች በበኩላቸው የቀረበው ዋጋ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ገልፀው ለሱም ማካካሻ ኢትዮቴሌኮም በውጭ ምንዛሪ የተወሰነው እንዲከፈለው ጠይቋል፤ የሳፋሪኮም ሀላፊዎች በበኩላቸው ድርጅታቸው ሀገር ውስጥ የተመዘገበ ስለሆነ በብር መጠቀም አለበት ሲሉ ኢትዮቴልኮም በበኩሉ መሰረተልማቶችን በዶላር ከፍሎ እንደሚያሰራ እና የውጪ ምንዛሪ እንደሚያስፈልገው ይገልጻል፡፡
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አና የቁጥጥር ከፍተኛ ኦፊሰር የሆኑት ማቲው ሀሪሰን ስምምነቱ በተለያዩ ምክንያቶች ቢዘገይም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ባለፈው ወር ስምምነት ላይ ይደረሳል ብሎ ሲጠብቅ እንደነበር ተናግሯል።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሀላፊው ለካፒታል እንደተናገሩት ጉዳዩን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው በያዝነው ወር መጨረሻ መፈታት ካልተቻለ ነገሩን ወደ ኢትዮጵያ ኮምኒኬሽን ባለስልጣን እንደሚወስዱት ገልጸዋል።ባለስልጣኑ በህጉ መሰረት ጣልቃ መግባት እና የማስማማት ስልጣን አለው፡፡