ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከ15 አመት በፊት በስደት ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ትብብር የተመሰረተው ኢሳት ለሁለተኛ ጊዜ ሊሰነጠቅ መሆኑ ታወቀ።
በጫካ ትግል ኤርትራ በረሃ ገብቶ የነበረው ግንቦት ሰባት ከአዲሱ የመንግሥት ለውጥ ጋር በተያያዘ ወደ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ ይፋ ባደረገው መሰረት ኢሳትን በባለቤትነት ያስተዳደር እነደነበር የሚታወወለቅ ነው። ነገር ግን ከአሁን በኋላ በሕዝብ እንዲተዳደር ፈቅጃለሁ ከማለቱ ጋር ተያይዞ ከፈተኛ ውዝግብ መነሣቱ የታወሳል።
ይሄንን ተከተሎ በተፈጠሩ ጠንካራ የሀሳብ ልዩነቶች የተወሰኑ የእሣት ጋዜጠኞች ተገንጥለው በመውጣት ኢትዮ 360 የተሰኘ ሚዲያ ከፍተዋል።
ለጥቂት ጊዜ የቀጠለው ኢሣት በአዲስ አበባና በውጭ ሀገር በሚገኙ ጋዜጠኞችና በአዲስ አበባ መዋቀር ስር እንዲተዳደር በሚፈልጉ መካከል በተነሳ ልዩነት በአሜሪካን ሀገር ክስ ተመሰርቶ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተላልፏል።
በዚህም መሰረት በስውር ስሙ አቶ ገድሉ ኪዳኔ (ዶ/ር አሸናፊ) መሪነት እንደሁም በሌላ በኩል ድርጊቱን በተቃወሙት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እና መሳይ መኮነንን ጨምሮ ሌሎች ጋዜጠኞችና የቴክኒክ ባለሙያዎችን በመወከል በዶ/ር ሰሎሞን የሚመራ ቡድን በአሜሪካን ፍርድ ቤት ሲከራከሩ ቆይተዋል። ክርክሩ የግንቦት ሰባት የቀድሞ የስውር አመራር አባልነት በሚታወቀው በእነ ዶከተር አሸናፊ ወይንም አቶ ገድሉ አሸናፊነት ተጠናቋል።
በመሆኑም ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና፣ መሳይ መኮነን፣ ወንድማገኝ ጋሻው፣ ፋሲል የኔዓለምን ጨምሮ የካሜራ እና የቴክኒክ ባለሙያዎች ከኢሳት ተነጥለው ኢሣት ኢንተርናሽናል የተሰኘ አዲሰ ሚድያ ይዘው ለመምጣት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ለማወቅ ችለናል።
በአዲስ አበባ በእነ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንደሁም በውጭ ሀገር ደግሞ በነ ዶ/ር አሸናፊ በሚተዳደረው ኢሳት በሌላ በኩል በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ጋዜጠኞችን መመልመል የጀመሩ ሲሆን ነባሮቹ የኢሳት ጋዜጠኞች በሌላ በኩል አዲሱን ኢሳት ኢንተርናሽናል በጥቂት ቀናት ውስጥ ይፋ እንደማይደረጉ ይጠበቃል።