በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ የሚመራው ሰላምና ልማት ማዕከል ፈቃዱ ተመለሰለት

በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ የሚመራው ሰላምና ልማት ማዕከል ፈቃዱ ተመለሰለት

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሰላምና ልማት ማዕከል የተባለው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት በኢትዮጵያ መንቀሳቀስ የሚያስችለው ፈቃድ እንደተመለሰለት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በፕሮሰር ኤፍሬም ይስሐቅ የሚመራው ተቋም ፈቃዱን የተነጠቀው “በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የሞራልም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ” የሚለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድንጋጌ ተላልፏል በሚል ነበር። ከህዳር 17 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ፈቃዱ የተሰረዘበት ሰላምና ልማት ማዕከል የስራ ፈቃዱ ተመልሶለታል። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንዳረጋገጠው በአዋጅ 1113/2011 አንቀጽ 88/3 መሰረት በሰርተፍኬት ቁጥር 2936 ሕጋዊ ፈቃድ አግኝቶ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው።

ተቋሙ እርምጃው የተወሰደበት ህዳር 15 ቀን 2014 ዓ.ም. አሰናድቶች በምስለ ስብሰባ የተካሄደው ውይይት በካናዳዊው ጋዜጠኛ ጄፍ ፒርስ አማካኝነት ይፋ ከተደረገ በኋላ ነው።

(ዶ/ር) እሌኒ ገ/መድህን አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስን ጨምሮ የውጭ ሐገራት ዲፕሎማቶች የተሳተፉበት ውይይት የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ላይ መወሰድ በሚገባው እርምጃ ላይ ያተኮረ ሲሆን ከህዝብ እና ከመንግሥት ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው ይታወሳል።

LEAVE A REPLY