ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች በተለያዩ የግል ባንኮች የከፈቷቸውን ሒሳቦች በአስቸኳይ እንዲዘጉ፣ ይህንንም ማድረጋቸውን የሚያረጋግጥ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ታዘዙ፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር በግል ባንኮች ውስጥ አካውንት ከፍተው ገንዘብ እያንቀሳቀሱ ነው ለተባሉ መሥሪያ ቤቶች በጻፈው ደብዳቤ፣ በግል ባንኮች ውስጥ ያላቸውን ሒሳብ ካልዘጉ ዕርምጃ እንደሚወሰድባቸውና ትዕዛዙን ያልፈጸመ መሥሪያ ቤት በጀት አይለቀቅለትም በማለት አስጠንቅቋል፡፡
በመንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው የፋይናንስ አስተዳደር ደንብ መሠረት፣ የመንግሥት ገንዘብ ወይም ገቢ የሚደረገው በብሔራዊ ባንክ ወይም ብሔራዊ ባንክ በሚወክለው ባንክ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
በዚህ ድንጋጌ መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለጊዜው የሰየመው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ብቻ መሆኑን የሚኒስትር ዴኤታው ደብዳቤ ያመለክታል ሲል ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
ሆኖም በአሁኑ ወቅት በርካታ የመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች የመንግሥት ገንዘብ ለማንቀሳቀስ በግል ባንኮች ሒሳብ በመክፈት ላይ መሆናቸውንና ይህንን ማቋረጥ እንደሚኖርባቸው ታምኗል፡፡