ቻይና በሰባት የኢትዮጵያ ኩባንያዎች ላይ እገዳ ጣለች

ቻይና በሰባት የኢትዮጵያ ኩባንያዎች ላይ እገዳ ጣለች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የወጪ ንግድ ላይ የተሠማሩት ድርጅቶች የታገዱት በጥራት ጉድለት ነው። ከታገዱት መካከል አለሙ ነጋ ፣ ጀማ ትሬዲንግ፣ አንለይ አድማሱ፣ ደሳለኝ ገብረሚካኤል፣ እና እድሜአለም እጅጉ ተጠቅሰዋል።

የቻይና ጉምሩክ ባለስልጣን ለእገዳው ምክንያት የሆኑት የምዝገባ ተለዋዋጭነት፣ ከደረጃ በታች የሆነ ምርት ማቅረብ፣ ደረጃውን ያልጠበቀ የምርት አስተሻሸግ እንዲሁም በሰሊጥ ምርት ላይ የታየ የጎጂ መድኃኒቶች መገኘት ነው ተብሏል።

ቻይና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በተመለከተ ከጥር ጀምሮ ይፋ ያደረገቻቸው አዳዲስ የጥራት ደረጃዎች አሉ። ኢትዮጵያ ቡናን ጨምሮ 18 አይነት ምርቶች ወደቻይና ትልካለች ሲል ሪፖርተር ዘግቧል።

LEAVE A REPLY