ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኦሮሚያ ክልል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያላስመዘገቡ 3,628 ተማሪዎች ተለይተው የ2014 ፈተናን በድጋሚእንዲወስዱ እድል እንደተሰጣቸው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በፀጥታ ችግር ውስጥ በመሆን የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያልመጣላቸው ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር ባሳለፈው የድጋሚ ፈተና ዕድል ተጠቃሚ ይሆናሉ ብሏል።
በሰባት ዞኖች ማለትም ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ እንዲሁም ምዕራብ ሸዋ ውጤት ያልመጣላቸው በሙሉ ከዘንድሮ ተፈታኞች ጋር ፈተናውን እንዲወስዱ ተወስኖላቸዋል።
በሰሜን ሸዋ ዞን 7 ወረዳዎች፣ በጅማ ፣ ምስራቅ ሸዋ እና ምዕራብ ሀረርጌ ሁለት ሁለት ወረዳዎች እንዲሁም በቦረና 3 ወረዳዎች፣ በምስራቅ ሀገርጌ 1 ወረዳም የድጋሜ ፈተና ከተፈቀደላቸው መካከል ይገኙበታል።
የድጋሜ ፈተናውን የሚወስዱት አጠቃላይ 3,628 ተማሪዎች መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።