የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ወድድር በዚህ አመት ከጁላይ 2-9 እንደሚካሄድ ተገለጸ

የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ወድድር በዚህ አመት ከጁላይ 2-9 እንደሚካሄድ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሰሜን አሜሪካ ኢትዮጵያንን በማሰባሰብ የሚታወቀው esfna ለሁለት ተከታታይ አመታት በኮቪድ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን አመታዊ ክብረበዓል በዚህ አመት ለመቀጠል መወሰኑ ተሰምቷል።

ከሁለት አመት በፊት በሚኒሶታ ግዛት በአሉን ለማክበር ተወሰኖ በኮቪድ ወረርሽኝ መስፋፋት መክንያት መሰረዙ ይታወቃል።

በዚህ አመትም በአሉን ለማዘጋጀት ተነስቶ የነበረውን ውዝግብ ቦርዱ በዛሬው እለት ካደረገው የአራት ሰዓታት አድካሚ ስበሰባ በኋላ ውሳኔ አሳልፏል።

9 በ 15 በሆነ የድምጽ ብልጫ ቦርዱ ውድድሩ በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ካፒታል ዋን (one) ስታድየም እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።

በስፖርታዊ ወደዳርና በባህላዊ ትዕይንቶች የሚደምቀው ክብረ በዓል ከጁላይ ሁለት ቀን እሰከ ጁላይ 9 ቀን ለአንድ ሳምንት እንዲቆይም ተወሰኗል።

ኢ ኤስ ኤፍ ኤን ኤ (ESFNA) በውጭ ሀገር የመኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ከ30 አመታት በላይ በየዓመቱ የሚያገናኝ ተቋም ነው።

ይህንን ሕዝባዊ ተቋም ለማፍረስ ሕወሃት መራሹ የኢሕአዴግ መንግሰትና ባሀብቱ ሸህ መሀመድ አላሙዲን በነ አቶ አብነት የሚመራ ሌላ ተለጣፉ ድርጅት በማቋቋም ከፍተኛ ጥረት ተደርጎበት እንደነበር ይታወሳል።

LEAVE A REPLY