ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የወልዲያ ከተማ አስተዳደር በከተማው ውስጥ የሚገኙ ሰርጎ ገቦችን ለመለየት እንዲቻል የከተማዋ ነዋሪዎችን በሙሉ መታወቂያ ሊቀር እንደሆነ አስታወቀ፡፡ በከተማው ውስጥ ካለው ሁኔታ አንፃር እየተለዩ የሚታሰሩ ግለሰቦች እንዳሉ የገለጸው የከተማ አስተዳደሩ አዲስ መታወቂያ የሚወስዱ ሰዎች ያላቸውን መታወቂያ ከከተማዋ ወሳኝ ኩነት መረጃ ጋር እንደሚያመሳክር ገልጿል፡፡
ለወራት በሕወሓት ቁጥጥር ሥር ከቆየች በኋላ በታኅሳስ ወር ላይ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በሆነችው ወልዲያ ሰርጎ ገቦች የቀድሞውን መታወቂያ መያዛቸውን ለሪፖርተር የተናገሩት የወልድያ ከተማ ከንቲባ (ዶ ር) ዳዊት መሰለ በዚህም ምክንያት የከተማው አስተደዳር የከተማዋን ነዋሪዎች መታወቂያ ለመቀየር ውሳኔ ማስተላለፉን ገልጸዋል፡፡
እንደ (ዶ/ር) ዳዊት ገለጻ ከዚህ ቀደም መታወቂያ ሲሰጥ የነበረው መረጃዎችን በመዝገብ ላይ በመጻፍ ብቻ የነበረ ሲሆን ይህም በቀበሌዎች መካከል የሚጣራበት ሁኔታ እንዳይኖር በማድረጉ የተለያዩ ቀበሌዎች ላይ ከአንድ በላይ መታወቂያ ያላቸው ሰዎች አሉ ሰርጎ ገብ የተባሉትን ሰዎች ማንነት አብራርተው ባይገልጹም የከተማዋ ነዋሪዎች መታወቂያ እንዲይዙ የሚያደርጉ የቀበሌ አመራሮች አሉ የሚል ጥርጣሬ እንዳለ አስረድተዋል፡፡ አሁን መታወቂያ የማደስ አገልግሎት እንዲቆም መደረጉን ገልጿል፡፡