ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በአጋቾቹ የአብንና የፋኖ አባል ነህ ተብሎ ተጠይቋል

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በአጋቾቹ የአብንና የፋኖ አባል ነህ ተብሎ ተጠይቋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከቀናት በፊት በፀጥታ ኃይሎች ከቤቱ ተወስዶ ለቀናት ያለበት ሳይታወቅ ከህዝብ ተሰውሮ እንደነበር ይታወሳል። ጋዜጠኛው እስከ ዛሬ የት እንዳቆየ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የገለፀ ሲሆን በጤናው ላይ አንዳች የደረሰ ነገር እንደሌለ አሳውቋል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ከኢድ አልፈጥር አንድ ቀን ቀደም ብሎ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በአጥር ዘለው አፍነው እንደወሰዱት ኢትዮጵያ ነገ ዘግባ እንደነበር ይታወሳል።

ላለፉት 8 ቀናት ማንነታቸው ባልታወቀ የፀጥታ አካላት ከመኖሪያ ቤቱ ታፍኖ የተወሰደው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከ ተለቆ ወደ ቤቱ መግባቱን ተረጋግጧል።

ጎበዜ ስለሁኔታው ለዋዜማ በሰጠው ማብራሪያ በመጀመሪያ የተያዘበት ሁኔታ ፍፁም ኢ-መደበኛ መሆኑንና አጋቾቹ ሲቪል ብቻ ሳይሆን የማይገመት ተራ አለባበስ ያላቸው ግን ደግሞ የታጠቁ ግለሰቦች በአጥር ዘለው ገብተው ለጥያቄ ትፈለጋለህ በሚል ይዘውት ወጥተዋል።

ከተወሰደም በኋላ የት እንደነበረ መለየት እንዳልቻለና ብቻውን በአንድ ቤት ውስጥ መቆየቱን በአቅራቢያው የቤተ ክርስቲያን ድምፅ ይሰማ እንደነበር ብቻ ገልጿል።

ከአጋቾቹ የቀረበለትን ጥያቄ በተመለከተ “የአብን እና የፋኖ አባል ነህ ወይ?” የሚል ጥያቄ ቀርቦለት እንደነበርና በቆይታው ምንም አይነት አካላዊ ድብደባ ወይም ጉዳት እንዳልደረሰበት እና ምግብ በአግባቡ ይቀርብለት እንደነበር አብራርቷል።

በመጨረሻም አይኑን በጨርቅ ሸፍነው ወደቤቱ መግቢያ በር እንዳደረሱት እና ጥለውት እንደሄዱ በተለይ ለዋዜማ በሰጠው መረጃ ገልጿል

LEAVE A REPLY