ሱዳን በወረራ በያዘቻቸው የኢትዮጵያ ግዛቶች የህዝብ ስብጥርን ለመቀየር እየሰራች ነው ሲሉ አቶ...

ሱዳን በወረራ በያዘቻቸው የኢትዮጵያ ግዛቶች የህዝብ ስብጥርን ለመቀየር እየሰራች ነው ሲሉ አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሱዳን የተወሰደው የኢትዮጵያ ግዛት በየትኛውም መመዘኛ እንደሚመለስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቀ፡፡ ሚሰስትሩ ይህ የተነገሩት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበበት ወቅት ነው ፡፡

አቶ ደመቀ ሱዳን ኢትዮጵያ በሰሜኑ የገጠማትን ችግር እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅማ ወረራ መፈጸሟን አንስተዋል። የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት ከመውረር ባለፈ የአካባቢውን ነዋሪዎች ማፈናቀሏንና የንብረት ውድመት ማድረሷንም ተናግረዋል፡፡

ባለችበት እንድትቆይ ንግግር መደረጉንና ኢትዮጵያም ይህንኑ ማድረጓን የገለጹት አቶ ደመቀ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግን ኢትዮጵያን አቋም ከማበረታታት ባለፈ የካርቱምን ድርጊት አለማውገዙን አስታውቀዋል፡፡

የሱዳን መንግስት ድንበር ጥሶ ወረራ ከመፈጸሙ ባለፈ ለህወሓት መሰረት በመስጠት ወደ ኢትዮጵያ ጥቃት እንዲሰነዘር እያደረገች ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ፤ ከሱዳን ጋር ያለትን ጉዳይ በሰላም እንዲፈታ ማድረግ ያለባትን ሁሉ እያደረገች እንደምትቀጥል አቶ ደመቀ ተናግረዋል፡፡
ከከፋ ጉዳት መለስ ባለ ሰላማዊ መልክ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ ጥረቱ እንደሚቀጥልና መንግስትም ይህንን እየተከታተለ እንደሆነ አቶ ደመቀ ጨምረው ተናግረዋል ።

LEAVE A REPLY