የከተማ አስተዳደሩ 25 ሺህ 491 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በእጣ አስተላለፈ

የከተማ አስተዳደሩ 25 ሺህ 491 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በእጣ አስተላለፈ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ40/60 ለ3ኛ ጊዜ እና በ20/80 14ኛ ጊዜ በድምሩ 25 ሺህ 491 ቤቶችን ለቆጣቢዎች በዛሬው ዕለት በይፋዊ ሥነ ሥርዓት አስተላልፏል፡፡

የእጣ ማውጣቱ ሥነ ሥርዓት ከንቲባ አዳነች አቤቤና ሌሎች አመራሮች ገለልተኛ ታዛቢዎች የተመዝጋቢዎች ተወካዮች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች በተገኙበት የተከናወነ ሲሆን፤ በተለይም በዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓቱ በልዩ ሁኔታ የቅድሚያ ተጠቃሚ የሚሆኑ ዜጎችን በአግባቡ የሚለይበትን አግባብ ጭምር ሂደቱን በማብራራት እና በቀጥታ ሥርጭት በማከናወን በግልፅነት መከናወኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

በዛሬው የዕጣ አወጣጣ ሥነ ሥርዓት ላይም የባለሦስት መኝታ ቤት ያልተካተተ ሲሆን ይህም ባለፈው ዙር ዋጋውን እስከ 1500 ቁጠባ ድረስ በማውረድ በማስተናገድ የቤቶች ቦርድ ፕሮግራሙን በመዝጋቱ በዚህ ዙር ለማስተናገድ አጠቃላይ ሲስተሙን የሚያዛባ በመሆኑ በቀጣይ በልዩ ሁኔታ የሚታይ መሆኑም ተገልጿል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ዓመታት በቤት ፕሮግራም ከ300 ሺህ በላይ ቤቶችን ሰርቶ ለተጠቃሚዎች ማስረከቡንም አስታውቋል።

LEAVE A REPLY