ተሀድሶ በትግራይ ከሽፏል ስል በሌሎች ክልሎች የተደረገ ተሀድሶ ተሳክተዋል ማለት አይደለም። ማንም ሰው መገንዘብ ያለበት በትግራይ ገዥ የሆነው ህወሐት ከከሸፈበት በሌሎች አካባቢዏች ደግሞ የባሰ ከሽፋል ማለት ነው።
ህወሐት ሀይለማሪያም ደሳለኝ ለኢትየጱያ ህዝብ በገቡለት ቃል መሰረት ሙሶኞችና ኪራይ ሰብሳቢዏች ሆዳሞች፣ ስልጣናቸው ተጠቅመው በዘመድ አዝማድና ደለዮች ህዝባችን የመዘበሩ ሌቦችና ሆዳሞች ከባድ እርምጃ እንወስዳለን ያሉትን፣ በህወት መንደር ሊሰራ አልቻለም። በአንጻሩ የህወሐት አመራር ጠ/ምንስቴሩ እናስወግዳቸው አለን ያሉዋቸው ክራይሰብሳቢዏችና ሙሶኞች እንዲሁም ጎጦኞች እንደማስወገድ ፈንታ፣ መሬት እንደጠራች አስመስለው በሚዲያ ህዝብ እያስደነቆሩ ከርመው ፣ በተጨባጭ የምንመለከተው ግን የበሰበሱ የህወሐት መዋቅር በህዝብ የተጠሉ ራሳቸውም ቤት ዘግተው የገመገመዋቸውና በህዝብ ሀብት የማያልቅ ቤት ፣ቁሳቁስ ፣ገንዘብ የሰበሰቡ ትጃሮች ወደ ህግ አቅርበው እንደመቅጣት ሽልማት እየሰጡ በስብሰው ካበሰበሰትና ካሳቃዩት አካባቢ እንደገና ወደ የማያውቃቸው ህዝብና አካባቢ በመዛወር ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ እርጥብ ቆዳ አንጥፉልኝ አይነት የውሼቱ ተሀድሶ እየተመለከትን ነው ። በመሆኑ ወደ የማያውቃቸው አከባቢ ተሰማርተዋል። በመሆኑ ህዝብ ይወቃቸው።
የተከበራቹ ወገኖች በሀወሐት መንደር እንተደሳለን የሚል መዝሙር ከተጀመረ ረጅም ጊዜ አሰቆጥራል ።ይህም መለስ ዜናዊ በነበረበት ጊዜ እስከአሁን ሰወስት ጊዜ በስብሰናል እንታደሳለን በማለት አካኪ ዘራፍ ብለው ነበር። ባለፉት ተሐድሶዏች ግን አፈጻጽማቸው ካሁን ተሀድሳቸው ልዩነት የለውም። ለዩነት አለመኖራቸው በምሳሌነት ለመጥቀስ፣
1 -በአላማጣ ፣በኮሮም ፣ በሙኹኒ፣ በማይጨው በተለያዬ የታሐድሶ መድረክ በመሱና ኪራይ ሰብሳቢነት የመልካም አስተዳደር ጠንቅ ናቸው የተባሉ ከ34 በላይ ባለስልጣናት በሀዝብ ተገምግመውና ተጠልተው ተባርረው ፣ የበሰበሰው አመራር ታማኝ በመሆናቸው በፈደራል መንግስት ቁልፊ ቦታ ተመድበው በለመዱት እየበዘበዙ ይገኛሉ።
2 . በሽሬ አውራጃ በከተማ ማዛገጃ ቤትና ዞን አስተዳደር ተመድበው ይሰሩ የበሩ 6 ከንቲባዏች፣ 4 የዞን አስተዳዳሪዏች እጅግ ቡዙ ወረዳ አስተዳዳሪዏች በህዝብ ጥለቻ ተባርረው፣ በመሉ በክልልና በፈደራል መንግስታት ተመድበው ምዝበራቸው ቀጥለውበታል።
3 . ከአከሱም 3 ከንቲባዏች 5 የዞን ባለስልጣናተ የአድዋ ከንቲባና መዋቅሩ፣ የተንቤን ዓብይ ዓዲ ከንቲባዏች አስተደዳሪዏች ከ45 ባለይ በሙሱና በቡልሽው አስተዳደራቸው ምክንያት ህዝብ ያባረራቸውከሽሬና ከራያ እንደተባረሩ ሁሉ በሌላ ቦታ ሄደው ተሽመው አገርን እያባላሹ ይገኛሉ።
4 .በመቀሌ ከተማ 10 ከንቲባዏችና በደርዞኖች የሚቆጠሩ መዋቅራቸው ተባርረው በሙሉ ለማለት ይቻላል በክልሉና በፈደራል ቁልፊ ቦታ ይዘው አገርና ወህዝብ እያጠፉ ይገኛሉ።
5 . ከህወሐት ማ /ኮሚቴ አባላትም በጉባኤተኛ አትመሩም ፣ሌቦች ናችሁ፣ ብቃትም የለቸው ተብለው የተባረሩ በሙሉ ለማለት ይቻላል፣ የጠ/ ምኒስቴር አማካሪዏች፣ የኤፈርት አመራር ፣አንባሳደርነት፣ የፓርላማ ተመራጮች የፈደራል ታላላቅ ቢሮዏች ለምዝበራ በሚመች ቦታ ተመድበው አገር እያባላሹ ይገኛሉ።
6 . የዘንድሮ የህወሐት የውሼት ተሀድሶውም ካለፉት ተሀድሰዏች በተመሳሳሊ የሀገራችንና የክልላችን አንጡራ ሀብት መዝብረውና ወረው ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ደልበው እያሉ ለአንድ አመት ያህል የመንግስት አበል እየበሉ 700 ሽህ አባል የተባለ እሱ በሳቸው ተገማግመው 24 ሰአት ሙሉ በሚዲያ ቢደሰኩሩም በተግባር ግን የተናገርነው እንዳንገላለጥ ከተገላለጥን ህወሐት ትጠፋለች በመሆኑ ተቻችለን እንለፍ ብለው የተማማሉ ይመስል እስከአሁን አንድ እርምጃም አልወሰዱም።
የወሰዱት እርምጃ ቢኖር የትግራይ ህዝብ በግልጽ የሚያውቃቸው ሆዳሞችና ሌቦች አዲስ አበባ አላቸው መደበቅያ ሄደዋል እንዳውም በበለጠ በሚበላ ቦታ ነው የተመደቡ።
በትግራይ ውስጥም መቀሌ የነበረ አክሱም ሽሬ ህሞራ ወይ ራያ የነበረ መቀለ ነው የተቀያየሩ።
ለምሳሌ ሁለት የፖሊስ ኩማንዶሮች ለ25 አመት ያህል የመቀሌ ህዝብ ያሳቃዩ የበዘበዙት ሁለት ኩማንደሮች አንዱ ወደ አክሱም አንዱ ወደሽሬ ተመድበዋል ይህ ነው የህወሐት እርምጃና ተሀድሶ። በመሆኑ በህወሐት ተሀድሶው ያለጥርጥ 100 % ከሽፍዋል።
የተከበራችሁ ወገኖቼ የዘንድሮ የጠ / ምኒስቴር ሀይለማርያም ተሀድሶ በህወሀት ብቻ አይደለም የከሸፈው ። የውሼት ተሀድሶው በባአዴን ፣በኦዴድ ፣በዴኸደን ፣በአጋር ፓርቲዏች ውሼቱ ስላልቻሉበት በሁሉም 100 % ከሽፋል ።
የተከበራችሁ ወገኖቼ ኢህአደግ እየመራው ያለው ስርአት በጠግን ጠግን ሊታደስ አይችልም ።ሊታደስ ከሆነ መሰረታዊ የአይዶሎጂ፣ የኢኮኖሚ ፖሊስ የአስተሳሰብ ለውጢ እንዲሁም በሁሉም አይነት ዲሞክራሲያዊ መርሆዏች ካላረጋገጠ ፣ የዜጎች ነጻነት፣ የህግ የበላይነት ካላደረገ ለውጥ አይመጣም።
20 / 5 / 2009 ዓ ም