ኢትዮጵያ በሶማሊያ የአየር ክልል መጠቀም አቆመች

ኢትዮጵያ በሶማሊያ የአየር ክልል መጠቀም አቆመች

ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓ.ም. በሶማሊያ የአየር ክልል ውስጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ካጋጠመው ክስተት ተከትሎ ኢትዮጵያ የሶማሊያን የአየር ክልል መጠቀም ማቆምዋን አስታወቀች።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስያ አገራት ለሚያደርጋቸው በረራዎች ይጠቀምበት በነበረው የሶማሊያ የአየር ክልል በኩል መብረር ማቆሙን እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከሶማሊያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አስተማማኝ የአየር ትራፊክ አገልግሎት ባለማግኘቱ እንደሆነ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን፤ “በዓለም አቀፍ አሠራር መሠረት እንደዚህ ዓይነት ነገር ሲያጋጥም ለሚመለከታቸው የሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣናት ሪፖርት እናደርጋለን። የቅዳሜውን ክስተት በተመለከተም ለሶማሊያና ለኢትዮጵያ የሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣናት ሪፖርት ተደርጓል” ሲሉ ተናግረዋል። ይሁንና እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ የተሰጠ ምላሽ አለመኖሩን አክለዋል። የቅዳሜ ዕለቱ ክስተት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሶማሊያ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የሚሰጠውን አገልግሎት አስተማማኝ ሆኖ እንዳያገኘው ማድረጉን አቶ መስፍን ጣሰው ” ይህ ክስተት ካጋጠመበት ማግስት እሁድ የካቲት 17/2016 ዓ.ም. አንስቶ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሶማሊያን አየር ክልል መጠቀም ለማቆም መወሰኑን አስታውቀዋል።
ይህንንም ተከትሎ “አማራጭ ለመጠቀም ወስነናል። ለዚህም ዋናው ምክንያት የቅዳሜ ዕለቱ ክስተት ነው። እዚያ በነበረው ሁኔታ፤ የአየር ክልሉ አስተማማኝ የአየር ትራፊክ አገልግሎት ስላላገኘንበት ለደኅንነት ስንል አማራጭ መንገዶች እየተጠቀምን ነው” ሲሉ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው በሰጡት መግለጫ አየርመንገዱ ወደ እስያ ለሚያደርጋቸው በረራዎችን የሚደረገው በጂቡቲ አየር ክልል በመጠቀም መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጂቡቲን የአየር ክልል እየተጠቀመ ያለው ተጨማሪ ወጪ በማያመጣ መልኩ እንደሆነም አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY