በባህር ዳር  የጸጥታ ሃይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች መፋለማቸው ተገለፀ

በባህር ዳር  የጸጥታ ሃይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች መፋለማቸው ተገለፀ

በአማራ ክልላዊ መስተዳድር መዲና ባሕርዳር ከትማና ዙሪያው በመንግስት የፀጥታ ኃይሎችና በፋኖ መካከል የተኩስ ልዉዉጥ ሲካሄድ እንዳደረ የከተማውነዋሪዎች ተናገሩ።

ሐሙስ የካቲት21አርብ አጥቢያ& “አባይ ማዶ” እና “ቀበሌ 14” እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከባድ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ ማደሩን የተናገሩት የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ይህንንም ተከትሎ አርብ ዕለት በከተማው ውጥረት ነግሶ መዋሉን እና ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በከተማው ሲስተዋል ማምሽቱን አርብ አመሻሽ ላይ ለኢትዬጵያ ነገ ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት አርብ ሙሉ ቀን በመላ ከተማዋ ምንም አይነት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዳልነበረ መስሪያ ቤቶችና አገልግሎት ሰጭ ተቁዋማት ተዝግተው መዋላችውን ሁኔታውን በስጋት እየተከታተሉ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ከትላንት ሀሙስ አመሻሽ እስክ አርብ ቀትር በኃላ በባህር ዳር ከተማ የነበረውን የተኩስ ልውውጥ በተመለከተ የአማራ ክልላዊ መንግስት የኮምንኬሽን ቢሮ ማምሻውን መግለጫ ሰጥቷል።

“ህግ የማስከበር ዘመቻዉ በተሟላ ሁኔታ እየተከናወነ ነዉ።” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫው በባሕርዳር ዙሪያ የመከላከያ ሠራዊትና የክልሉ የፀጥታ ኃይል በጋራ በመሆን ሰርጎ የገባዉን ጽንፈኛ ቡድን በመፈለግና በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲንቀሳቀሱ ነበር ያለው መግለጫው በአሁኑ ሠዓት ሙሉ በሙሉ ባህርዳር ከተማና አካባቢዉ ከጽንፈኛ ቡድኑ ጸድተዋል። እነዚህ ጽንፈኛ ቡድኖች የጸጥታ ሀይሉን ጥምረት መቋቋም አቅቷቸዉ ሙትና ቁስለኛ ሁነዉ የያዙትን መሳሪያ ሳይቀር እያንጠባጠቡ ሸሽተዋል።

መከላከያ ሰራዊት የሚሹና እና የተደበቁ ጽንፈኛ ሀይሎች በያሉበት እያሰሰ ከተደበቁበት ጉሬ እያወጣ የክልላችን ሰላም ሙሉ በሙሉ ወደነበረበት ለመመለስ በጥሩ ወኔ እና ቁመና ላይ ይገኛል። ብሏል የክልሉ መንግስት ኮምንኬሺን ቢሮ መግለጫ።

በዚህ ከሐሙስ የካቲት 21ቀን እንስቶ በነጋታው የካቲት 22ቀን 2016 ቀኑን ሙሉ በባህርዳር ከተማ ውስጥ እና በከተማው ዙርያ ሲካሄድ በዋለው ፍልሚያ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ስለደረሰ ጉዳት እና ስለደረሰ ውድመት የክልሉ መንግስትም ሆነ የአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር ኮማንድ ፖስት የሰጠው መግለጫ የለም።

የፋኖ ታጣቂዎች በበኩላቸው የአድዋ ድል ዋዜማ ላይ በርካታ የመንግሥት ታጣቂዎችን በመደምሰስ ብዛት ያለው መሳሪያ በመማረክ የተሰጣቸውን ግዳጅ መፈፀማቸውን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY