ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ለማሽማግል ፍቃደኛ ነኝ” ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ለማሽማግል ፍቃደኛ ነኝ” ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን

በሶማሊያ እና  በኢትዮጵያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ለመሽምገል የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ፍቃደኛ መሆናቸውን ለሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ እንደገለፁላቸው ተነገረ።

በ3ኛው አንታሊያ ዲፕሎማሲ መድረክ ላይ የሶማሊያን ልዑካን ቡድን በመምራት የተገኙት የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ከፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ጋር ተገናኝተው ባደረጉት ውይይት ቱርኪዬ ሶማሊያን በተለያዩ ዘርፎች ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት እና በተለይ በመከላከያ ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥተው መወያየታቸው ታውቆል።

በተጨማሪም በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን አለመግባባት ለመቅረፍ በማንኛውም የሽምግልና ጥረት ላይ ለመሳተፍ ቱርኪዬ ያላትን ዝግጁነት ለሶማሊያ ፕሬዚዳንት እንዳሳወቁዋቸው የቱርኪ ብሄራዊ መከላከያ ሚኒስትር ያሳር ጉለር፣ አስታውቀዋል።

በሁለቱ ሀገራት መሪዎች ውይይት ላይ የቱርኪ ብሄራዊ መከላከያ ሚኒስትር ያሳር ጉለር፣ የሀገሪቱ የብሄራዊ መረጃ ድርጅት ሃላፊ ኢብራሂም ካሊን እና የፕሬዚዳንቱ ዋና አማካሪ አኪፍ ካጋታይ ኪሊች በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል። በተያያዘ ዜና የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ዑመር ጉሌህ በቱርኪዬ በመካሄድ ላይ ባለው የሶስተኛው አንታሊያን ዲፕሎማሲያዊ መድረክ ላይ ለመካፈል አንካራ ገብተዋል።

አርብ የካቲት 22ቀን2016 የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን የጅቡቲ አቻቸው ከፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኦሜር ጉሌህ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ተወያይተዋል።
ባለፈው ሀሙስ የካቲት 21ቀን የጀመረው ሶስተኛው አንታሊያን ዲፕሎማሲያዊ መድረክ ወደ 4,500 የሚጠጉ ሰዎች የተሳተፉበት ሲሆን ከነዚህም መካከል 19 የሀገር መሪዎች፣ 73 ሚኒስትሮች እና 57 አለም አቀፍ ተወካዮች ይገኙበታል።

LEAVE A REPLY