በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማዳበሪያ በ20ሺህ ብር እየተሸጠ ነው

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማዳበሪያ በ20ሺህ ብር እየተሸጠ ነው

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ባለመከፈሉ የትምህርትና የህክምና አገልግሎት መስተጓጉለሉ እንዲሁም በተድራጀ ሁኔታ የመንግሥት የህዝብ ገንዘብ እየተመዘበረ መሆኑ ተገለፀ።

በቅርቡ የተመሰረተውየማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባላት« የመንግሥት ሠራተኞችን ደሞዝ የሚያሳጣ መዋቅር መኖር የለበትም በሚል
የመንግስትና ህዝብ ሀብት መመዝበር ለማስቆም የተጠናከረ እንቅስቃሴ ለመጀመር ያደሩጉት ጥረት እንዳልተሳካ ገልፀዋል።

በአዲሱ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማዳበሪያን በተመለከተ የተቀናጀ የጥቅም ሰንሰለት በመዘርጋት ከፍተኛ ዘረፋ እየተፈፀመ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በመንግሥትና በማህበራት እጅ 4ሺህ ብር የነበረው አንድ ኬሻ ማዳበሪያ በነጋዴዎች እጅ እስከ 20 ሺህ ብር እየተሸጠ ይገኛል ተብሏል።

የፀጥታ አካላት ይህንን ህገወጥ ዝርፊያ እያዩ በዝምታ ማለፋቸው ዝርፊያው እንዲባባስና የማህበረሰቡ ኑሮ ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች እንዲደረግ በር ከፍታል ሲሉ አስተያየት ስጭዎቹ ተናግረዋል፡፡

የክልሉ መንግስት በበኩሉ ይህን ምዝበራ ለማስቀረት እየሰራሁ ነው ብሏል ። ከህዝብ በደረሰኝ ጥቆማ መሰረት በማድረግ የነዋሪውን ለወራት የዘለቀ ጥያቄን ለመመለስ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የገለፀው የክልሉ መንግስት ሙስናን ለመከላከል በቅንጅት በተሰራው ሥራ ያለአግባብ ሊከፈል ከነበረ ደመወዝ፣ ከኦዲት ጉድለት፣ ከመሬትና ሌሎች ምክንያቶች ጋር በተያያዘ ሊመዘበር የነበረ 165 ሚሊዮን የሚደርስ የመንግስት እና የህዝብ ሀብት ማዳን መቻሉን የክልሉ የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ቢሮ አሳውቋል።

LEAVE A REPLY