በሀረር ከተማ በህገ ወጥቤቶችና ግንባታዎች         በግብረኃይል  እየፈረሱ ነው

በሀረር ከተማ በህገ ወጥቤቶችና ግንባታዎች         በግብረኃይል  እየፈረሱ ነው

•⁠ ⁠ነዋሪዎች ከፖሊሶች ጋርተጋጩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከዛሬ የካቲት 25ቀን2016 ጀምሮ የሐረሪክልላዊ መንግስት ህገወጥ ቤቶችን እና በመሬት ወረራ የተያዙ መሬቶችን የማስመለስ ተግባር ለማከሄድ ግብረሃይል አቁዋቁሞ ወደስራ መግባቱን ተከትሎ ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸው ተሰማ። 

የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ሊደግፈው ይገባል ሲል የክልሉ መንግሥት የማፍረስ ዘመቻውን ከመጀመሩ በዋዜማው ጥሪውን  አቅርቦ ነበር ያሉት የሐረር ከተማ ነዋሪዎች ሆኖም በክልሉ የተዋቀረው ግብረኃይል ለበርካታ አመታት በነዋሪዎች የተያዙ ይዞታዎች ላይ የተገነቡ ቤቶችንም ለማፍረስ መሞከራቸው ነው ከነዋሪው ጋር ያጋጫቸው። ሲሉ ለኢትዮጵያ ነገ ዘጋቢ ተናግረዋል

ክልሉ  መንግስትህዝቡበተለያዩ መድረኮች ከአነሳቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ በክልሉ ትምህርት ቤቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የቱሪዝም ስፍራዎችና የአርሶ አደር መሬቶች ላይ እየተከናወኑ ያሉ ህገ ወጥ የቤት ግንባታዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት በጠየቀው መሰረት ነው ወደ ሥራ የገባሁት ማለቱን ያስታወሱት ነዋሪዎች በኢንቨስትመንት ተወስደው ለረጅም ጊዜያት ያለምንም ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ታጥረው የቆዩ መሬቶች  ለሶስተኛ ወገን  ለማስተላለፍ የተለያዩ የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች የመሬት ደላሎች ጋር  በመጣመር ሲንቀሳሱ  ተስተውለዋል።

በክልሉ የተለያዩ ቢሮዎችና ከፖሊስ እና ደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት የተወጣጡ የአፍራሽ ግብረሀይሉ  አባላት መውሰድ የጀመሩት እርምጃ አድሎ የታከለበትና ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ነው ብለው ያመኑ የከተማው ነዋሪዎች ናቸው ድርጊቱን በመቃወም ከክልሉ ፖሊስ ጋር መጋጨታቸውን ነው ምንጮች ለኢትዮጵያ ነገ የገለፁት።  ይህንኑ ዛሬ ሰኞ የካቲት 25ቀን2016 ረፋድ ላይ  በሐረር ከተማ የተፈጠረው ግጭትና  ውጥረት ተከትሎ የሐረሪ ክልላው መንግስት  መግለጫ  አውጥቶል።

የክልሉ መንግስት በዚሁ መግለጫው የህገወጥግንባታ የመሬት ወረራን ለበተመለከተ የተጀመረው ንቅናቄ የተቀመጠለትን ግብ ይመታል። ለህግ ተገዥ ባልሆኑ ህገ-ወጥ አካላት ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል፣ የክልሉ መንግስት ለሰላም እና የህግ በላይነት መከበር የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል።ሲል እስጠንቅቁዋል።

LEAVE A REPLY