ከኤርትራ ጋር ሌላ ዙር ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ተሰግቷል

ከኤርትራ ጋር ሌላ ዙር ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ተሰግቷል

የኢትዮጵያ መንግስት የአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ውሳኔዎችን ሳያከብር የኤርትራ ጦር የያዘውን የባድመና ዙርያውን ያሉ ቦታዎችን ለማስለቀቅ ከሞከረ ወደ ሌላ ዙር ጦርነት እንዳያመራ ያላቸውን ስጋት በርካታ እስተያየት ስጭዎች እየተናገሩ ነው። 

የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም  በቅርቡ በሰጡት ቃለምልልስ እንደገለፁት «አወዛጋቢ ቦታዎች» ባሏቸው እና ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች የሚገኙ  ከፌደራል መንግስት ውጭ የሆኑ ታጣቂዎችን ለማስወጣት እየተሰራ ነው ብለዋል።  

የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብረሃ በላይ በቅርቡ በኤርትራ ሰራዊት የተያዙ ቀሪ አካባቢዎችን ለመለየት እና መፍትሔ ለመስጠት እየተሰራ ነው ሲሉ የተናገሩትን ተከትሎ ነው የተለያዩ የህብረተሰብ አባላት ስጋታቸውን እየገለፁ ያሉት።

በጦርነቱ የተፈናቀሉትንም  ወደቀያቸው ለመመለስ የፌደራሉ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን። ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ እስካሁን  በተያዘለት ግዜ ባይሳካም፥ ጥረቶች መቀጠላቸውን አብረሃ በላይ  ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። 

ባለፉት ሁለት አመታት የወልቃይት ጠገዴ እንዲሁም የሴቲት ሁመራ አካባቢ እያስተዳደሩ ያሉ ወገኖችን ከስልጣን እንዲወገዱ ህወሓት መራሹ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሲጠይቅ ነበር። 

በዚህ ሳምንት የአፍሪካ ሕብረት ተወካዮች በተገኙበት፥ በፕሪቶሪያው ውል አፈፃፀም ዙርያ ውይይት ለማድረግ ዕቅድ መያዙን  የትግራይ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ገልጿል። በውይይቱም በተለይም ባልተፈፀሙ  የስምምነቱ ነጥቦች ላይ ምክክር  እንደሚደረግ ለዚህም በመዘጋጀት ላይ እንደሆኑ ታውቆል።

LEAVE A REPLY