ማይክ ሐመር በአማራና በኦሮሚያ ክልል  ያሉ ግጭቶችን ለመምከር ወደ አዲስ አበባ  ሊመጡ ነው 

ማይክ ሐመር በአማራና በኦሮሚያ ክልል  ያሉ ግጭቶችን ለመምከር ወደ አዲስ አበባ  ሊመጡ ነው 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአሜሪካ መንግስት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ማይክ ኃመር  በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራይ ክልላዊ መንግስት  መካከል በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በሚካሄደው ስትራቴጂካዊ ግምገማ ላይ ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው። 

ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር በአዲስ አበባ ከማርች 7 ቀን 2024 እስከ መጋቢት-13/2024 ባለው ጊዜ  ውስጥ በፌደራል መንግስቱ እና በሕወሐት መካከል የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ ስለሚወሰዱ ተግባራት፣ አፈፃፀም፣ የተፈጠሩ አለመግባባቶች እና ቅሬታዎችን እልባት ለመስጠት የሚካሄድ ስብሰባ ነው ላይ ለመሳተፍ ነው ሲል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አመልክቷል ።

መግለጫው ልዩ ልዑኩ ከአዲስአበባ ቆይታቸው በኃላ   ወደ ለንደን እና ሮም  ተጉዘው እስከ ማርች 20/2024 ድረስ የሚዘልቅ የሥራ ጉብኝት ፕሮግራም እንዳላቸው እስታውቆል።

“ጠመንጃዎቹ ጸጥ ቢሉም ውጊያ ቢቆምም ፣ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ ኢመደበኛ አደረጃጀትን የማፍረስ እና የመልሶ ማቋቋም ተግባራትን ጨምሮ ዘላቂ ሰላም ለማግኘት አስፈላጊ የሆኑ ተጨማሪ እርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልጋል። በአድሎ የፀዳ የሽግግር ፍትህ ሂደት በቀጣይነት የሚወሰድ እርምጃ መሆኑን  ከማረጋገጥ በተጨማሪ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀድሞ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማስቻል የተፋጠነ እንቅስቃሴዎች ሊወሰዱ ይገባል  ”ሲል የስቴት ዲፓርትመንት ያወጣው መግለጫ አስታውቀዋል። 

ከዚሁ ጋር በተያያዘም አምባሳደር ማይክ ሀመር ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር “በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የተፈጠረውን አለመረጋጋትና ወታደራዊ ግጭቶችን ለማስቆም በሚደረገው ጥረት ዙርያ  ለመወያየት እንዲሁም ሰፋ ያሉ ክልላዊ ጉዳዮችን ለመገምገም” ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ለመምከር ፕሮግራም እንደተያዘላቸው የአሜሪካ ውጭ ገዳይ መስሪያቤት እስታውቆል።  

በአፍሪካ ህብረት እደራዳሪነት የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ  ይህ በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚካሄደው    “ስትራቴጂካዊ ግምገማ”   የመጀመሪያው ነው።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአፍሪካ ህብረት  ስብሳቢነት ብቻ ስምምነቱን በተመለከተ ከፌዴራል መንግስት ጋር ለመወያየት መወሰኑን አሳውቆ “መጪዎቹ ውይይቶች የሚከናወኑት በአፍሪካ ህብረት ፓነል ብቻ ነው” ሲል የክልሉ አስተዳደር ጠንከር ያለ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር።

በፌዴራል መንግስት እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መካከል ከፕሪቶሪያ ስምምነት በተሟላ  ሁኔታ ተፈፃሚ ከማድረግ ጋር  በተያያዘ በተለይም በምዕራብ ትግራይ እና በደቡባዊ ትግራይ ክፍሎች ያለው ሁኔታ ላይ፣ አሁንም እንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ከጎረቤት አማራ ክልል በመጡ ከመንግስት ጋር ግንኙነት  ያላችው ሃይሎች የተያዙ  ከመሆኑም በላይ ተፈናቃዮች  ወደቀድሞ ቀያቸው መመለስ እና እንዲሁም በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች የኤርትራ ኃይሎች መውጣት መዘግየትን እስመልክቶ እንደሚመክሩ ታውቆል።

ሁለቱ ወገኖች በትግራይ ክልል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ላለው ከባድ ድርቅ እና የትግራይን ታጣቂ ሃይሎች ትጥቅ የማስፈታት፣  ልዩ ኃይልና የአካባቢ ሚሊሻ እደረጃጀቶችን የማፍረስ እና የመዋሃድ ሂደት መዘግየት ላይ  እና በክልሉ ባለው ከባድ ድርቅ አዝጋሚ ምላሽ ላይ ልዩነት አላቸው።

እ.ኤ.አ.የካቢኔ አባላት የፕሪቶሪያ ስምምነት ትግበራ ያለውን እድገት ለመገምገም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት በጌታችው ረዳ ከሚመራ የልዑካን ቡድን እና ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተዋል።

ምንም እንኳን የፌደራል መንግስት በስብሰባው ውጤት ላይ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ቢቆጠብም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ በምዕራብ ትግራይ አብዛኛው የአካባቢው ነዋሪ  ተፈናቅሎ ባለበት ሁኔታ በአካባቢው ህዝበ ውሳኔ የማካሄድ ሃሳብን በመቃወም ፌዴራል መንግስት የተያዘው አቋም ተቀባይነት የለውም የሚል አቁዋሙን በተደጋጋሚ ይፋ አድርጓል።

ከሁለት ቀናት በፊት የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ ከምእራብ ትግራይ የተፈናቀሉ ሲቪሎች ወደ ቤታቸው ለመመለስ  መንግስት እቅድ ማውጣቱን አስታውቀዋል። እንደ ዶክተር አብርሃም ማብራርያ “በምዕራቡ  ትግራይ አካባቢዎች ፣ በቀጥታ የበጀት ድልድል እና በአካባቢው ውደ ቀድሞ ሁኔታው   ለመመለስ ጊዜያዊ አስተዳደራዊ መዋቅርን ለማቋቋም የፌደራል መንግስት እቅድ ማውጣቱን አሶታውቆ ነበር።

በኢትዮጵያ መንግስትና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል ለሁለት ዓመታት የቆየውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ያስቆመውን የፕሪቶሪያ ስምምነት ገቢራዊነት ላይ አሸማጋዩ የአፍሪካ ህብረት አፈጻጸሙን አዲስ አበባ ውስጥ ሲገመግም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአውሮጳ ኅብረት፣ ኢጋድ እና ዩናይትድ ስቴትስ በታዛቢነት ሂደቱን ይከታተላሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

LEAVE A REPLY