ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በደቡባዊ ኢትዮጵያ ክልል ከጋርዱላ እና አሌ ዞኖች የተውጣጡ 285 የጉልበት ሠራተኞች በአማራ ክልል በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አካባቢ የደንምንጣሮ ስራ ለመስራት በጉዞ ላይ እያሉ “በታጣቂ ቡድኖች” መታገታቸውን አስታወቋል።
የምክር ቤቱ ሊቀመንበር አቶ ብርሃኑ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ድርጊቱ የተከሰተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን የደን ምንጠራ ስራ ጨረታ ማውጣቱን ተከትሎ በክልሉ የሁለት ዞኖች ነዋሪ የሆኑ 285 የሚጠጉ የጉልበት ሰራተኞች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሀይቅ በአካባቢ የሚገኙ ዛፎችን መቁረጥና የምንጠራ ሥራ ለማከናወን ወደ ፕሮጅክቱ እያመሩ እንዳለ መታገታቸውን ተነግረዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፕሬሽን ያወጣውን ጨረታ ያሽነፈው ለኒኮትካ ኮንስትራክሽን እና ትሬዲንግ ሊሚትድ ስራ ለማስጀመርም በጋርዱላ ዞን ከሚገኘው የዴራሼ ወረዳ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር የዛፍ መቁረጥ ስራ ልምድ ያላቸውን ሰራተኞች ለመቅጠር ስምምነት መሰረት በድምሩ 285 ሰራተኞች ከዴራሼ ወረዳ 246 ሰራተኞች ከ39 ደግሞ ከአሌ ዞን የተውጣጡ ግለሰቦች ተቀጥረዋል።
ሰራተኞቹ ድርጅቱ ባዘጋጀላቸው ስድስት የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች ወደ ስራ ቦታው እንዲጓዙ ተደርጓል። ነገር ግን አማራ ክልል ሲደርሱ የ 285 ሰራተኞች ቡድን በክልሉ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ “በታጣቂ ቡድኖች” በመንገድ ላይ ታግቷል ሲል ምክር ቤቱ ገልጿል።
በአፈናው ዙሪያ ያለው ትክክለኛ ቦታ እና ሁኔታ በአሁኑ ወቅት ግልጽ አይደለም ሲል የጋርዱላ ዞን ምክር ቤት ድርጊቱን አጥብቆ አውግዟል ፣ “ሰራተኞቹ ንፁሀን ዜጎች ነበሩ፣ በቀላሉ ወሳኙን የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ልማት ላይ ጉልበታቸውን ለማበርከት የሚጓዙ ናቸው” ብሏል። ምክር ቤቱ ሰራተኞች በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የመስራት እና ሀብት የማፍራት እና የመጓጓዝ መብት እንዳላቸው እና ከሰራተኛ ስራ ውጪ “የተለየ ተልዕኮ የላቸውም” ሲልም በአስቸካይ እንዲለቀቁ ጥሪ አድርጉዋል። ምክር ቤቱ በመግለጫው እገታው የተካሄደው መቼ እንደሆነ አልገለፀም።