ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ግንባታው የተጀመረበት 13አመት የሚሞላው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚጠናቀቅበት ጊዜ መራዘሙ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።
አስተያየት ሰጭዎች ይህ ግዙፍና ሁሉንም ኢትዩጵያዊ በአንድነት ያስተሳሰረ ፕሮጀክት ለመጠናቀቅ ከተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እልተጠናቀቀም። ሆኖም ሌት ተቀን እየተሰራ ዘጠና አምስት በመቶ መጠናቀቁን ከስማን ወራት ተቆጥረዋ። በእርግጥ መቼ ነው የሚጠናቀቀውና ሁሉም ተርባይኖች ኃይል ይሚያመነጩት? ሲሉ በርካታ ኢትዬጵያውያን ይጠይቃሉ።
አንዳንድ እስተያየት ሰጭዎች በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት በአለም ላይ የተገነቡ ግዙፍ ግድቦች የግንባታ እድሜ በአማካይ በ 10 አመት ውስጥ የተጠናቀቁ ናቸው በማለት ለምሳሌ ዘሥሪ ጎርጅ ዳም የተባለው ቻይና የገነባችው ግድብ የግንባታ ሥራው በ1994 ተጀምሮ በ2006 ነው የተጠናቀቀው። የፈጀው ድፍን አስራ ሁለት አመት ነው።
ሌላው የአለማችን ግዙፍ ግድብ በአሜሪካ የተገነባው ግሌን ካንዬን ዳም ሲሆን በ1956 ተጀምሮ በ1966 በእስር አመት ውስጥ ነው የተጠናቀቀው። በግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ የተገነባው የታላቁ የአስዋን ግድብ ግንባታው በ1960 ተጀምሮ በ 1970 የተጠናቀቀ ሲሆን በግንባታው ጊዜ ወደ 10 ዓመታት ገደማ መጠናቀቁን ያስታወሱ ለኢትዬጵያ ነገ አስተያየት የሰጡ ስማችን አይገለፅ ያሉ አስተያየት ስጭ (ብራዚል / ፓራጓይ) የተገነባው የኢታይፑ ግድብ ግንባታ በ 1975 ተጀምሮ በ 1984 ለማጠናቀቅ 9 ዓመታት ያህል ፈጅቶበታል።
የእኛ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ጫና ሲደርስብን ከፍተኛ ዘመቻ ሲካሄድበት ይህንንሁሉ ጫና ተቆቁሞ የኢትዬጵያ ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ገንዘቡን ያፈሰስበት የታለቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በ 2011 ተጀምሮ በ 2024 አሁን አስራ ሶስተኛ አመቱን ይይዛል። አሁንም መንግስትና ተጨማሪ ገንዘብ ለመስብሰብ ስትራቴጂ አውጥቶ ሊንቀሳቀስ ነው እንጂ የግድቡ መጠናቀቅ መቼ እንደሚሆን እያውቅም የዚህ ግድብ ግንባታ ለዚህ ትውልድ ዳግማዊ አደዋ ነውና መንግስት ፕሮጅክቱን በማጠናቀቅ በታሪክ ስሙን በወርቅ ቢፅፍ መልካም ነው። ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል። en