የኬንያው ክራውን ትራንስፖርት ማዕቀብ                   ተጣለበት

የኬንያው ክራውን ትራንስፖርት ማዕቀብ                   ተጣለበት

የኬኒያው የህዝብ ማመላለሻ አውቶቢስ ኩባንያ ላይ እህት ኩባንያው ሐላል ኮሚዲቲ ሊሚትድን ጨምሮ 16 ኩባንያዎችን ለአልሸባብ ተግባር በገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል በሚል  የአሜሪካ መንግስት ማዕቀብ እንደጣለችባቸው አስታወቀች።

የኬንያው ክራውን የህዝብ ትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማራው  ኩባንያ የታጣቂዎቹን ሎጅስቲክስ ተግባር ይደግፋል ያለው የአሜሪካ መንግስት መግለጫ  የሽብር እንቅስቃሴዎችን የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ የገንዘብ ዝውውር ማካሄጃ መስመሮችን እና አካላትን ለማስወገድ ከአካባቢው  አጋሮች ጋር ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። 

“የዛሬው እርምጃ የሶማሊያ መንግስት በአልሸባብ ላይ የሚያደርሰውን ኢኮኖሚያዊ ጥቃት ለመደገፍ የገንዘብ ግምጃ ቤት ያለው ዘርፈ ብዙ ጥረት አካል ነው።

ይህንን ገዳይ አሸባሪ ቡድን ለማዋረድ ዘመቻ ካደረጉት ሶስት ምሶሶዎች አንዱ ነው” ሲሉ የሽብር እና የፋይናንሺያል ኢንተለጀንስ ዋና ፀሀፊ ብራያን ኢ. ኔልሰን ተናግረዋል ።

ማዕቀቡ የተጣለባቸው ግለሰቦች እና አካላት በአልሸባብ አላማን ለማሳካት በሚሊዮኖች የሚገመት ገንዘብ በተለያዩ የንግድ ድርጅቶች ን በማቋቋም ገቢ በማሰባሰብ እና በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ተግባር ተሳትፈዋል ተብሏል። 

“የዛሬው ማዕቀብ ከተጣለባቸው   ግለሰቦችና አካላት እንዲሁም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ 50 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ በግል ወይም ከሌሎች የታገዱ ሰዎች ጋር በሽርክና የሚሰሩ  ባለአክሲዬኖች ንብረቶች እና ጥቅሞች  በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ያሉ ወይም የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች በቁጥጥር ስር ውለው ንብረታቸው እንዲታገድ  ለውጭ ሀብት ቁጥጥር ቢሮ ሪፖርት ማድረግ አለባቸው” ብለዋል ። en

LEAVE A REPLY