መንግሥት የዋጋ ግሽበትን ለማረጋጋት እርምጃ እየወሰደ ነው – ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

መንግሥት የዋጋ ግሽበትን ለማረጋጋት እርምጃ እየወሰደ ነው – ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መንግሥት የዋጋ ግሽበትን ለማረጋጋት  የፖሊሲ እርምጃዎችን እየወሰደ  መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ።

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የመግዛት አቅማቸው ዝቅተኛ በመሆኑ የዋጋ ግሽበት በሚፈጥረው ጫና ተጎጂዎች ሆነዋል።

በመሆኑም የዋጋ ግሽበትን ለማረጋጋት መንግሥት የተለያዩ የመፍትሔ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል።

በመሆኑም መንግሥት ከአገር ውስጥ ባንኮች በተለይም ከማዕከላዊ ባንክ የሚወስደውን የብድር መጠን እንዲቀንስ ማድረጉን አስታውቀዋል።

በምግብ ሸቀጦች ላይ ያለውን የዋጋ ግሽበት በዋናነት ለመፍታት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግና የንግድ ሥርዓቱን ማሻሻል መሆኑንምተናግረዋል። በዘላቂነት የዋጋ ግሽበትንም ሆነ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የዜጎችን የመግዛት አቅም (ገቢ) የማሳደግ፣ የምርት ዋጋ ላይ ትርጉም ያለው የዋጋ ቅነሳ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ አሁንም ለውጦች አሉ ብለዋል። en

LEAVE A REPLY