ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ቀናት ባደረገው የቁጥጥር ስራ ግምቱ 40 ሚሊየን ብር የሚሆን ቆርቆሮ እና ግምታዊ ዋጋው 16 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሆነ ቶንዲኖ ብረት መያዙን አስታወቀ።
የንብረቶቹ አጠቃላይ ግምት በድሞሩ 56 ነጥብ 5 ሚሊዬን ብር የሚገመት በሀሰተኛ የጉምሩክ ሰነዶች ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጉምሩክ ኮምሽን አሳወቀ፡፡
በሀሰተኛ ሰነድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እነዚህን እቃዎች ሲያዘዋዉሩ የተገኙ ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆኑን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቆል።en