ብጹዕ አቡነ መቃሪዮስ እርስ በእርስ መገዳደል                 ...

ብጹዕ አቡነ መቃሪዮስ እርስ በእርስ መገዳደል                  እንዲቆም ጥሪ አደረጉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዳርቃይ ወረዳ በሰሜኑ ጦርነት የሃይማኖት ተቋማት ድረስ ከፍተኛ ውድመት የደረሰባቸውንየእምነት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት እና የአካባቢውን ሰላም ማስጠበቅ ላይ ያለመ ፕሮግራም ተካሂዷል። 

በፕሮግራሙ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ መቃሪዮስ   በአደረጉት ንግግር የወረዳው ነዋሪዎች በጦርነቱ ከፍተኛ ችግር እንደደረሰባቸው በማስታወስ የእርስ በእርስ መገዳደልን አቁመው፤ ሰላማቸውን በመጠበቅ ከችግር ለመውጣት እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል። 

 የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው ጦርነት ኑሮን ከዜሮ እንዲጀምሩ አድርጓል፤ አሁንም ገና ከችግር አለመውጣታቸውንም አስገንዝበዋል። ጦርነት አንደማይፈልጉም ነው የተናገሩት።

ጦርነት ካደረሰባቸው ችግር ለመውጣት ጥረት ላይ መኾናቸውን ያነሱት ነዋሪዎቹ መንግሥት የወደሙ የጤና፣የውኃ፣የትምህርትእናመሰልተቋማትየትምህርት እና  መሰልተቋማትንመልሶየመገንባት ሥራ እንዲሠራ፤ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ወገኖችንም እንዲረዳ በስነስርአቱ ላይ ጠይቀዋል። en

LEAVE A REPLY