የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከ100 ሺህ በላይ  ጦር  ማስናበቱን አስታወቀ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከ100 ሺህ በላይ  ጦር  ማስናበቱን አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከ100,000 በላይ የቀድሞ ታጋዮችን ከሰራዊት እባልነት ማሰናበቱን አሳወቀ።

በመጀመርያው ምዕራፍ ከትግራይ ክልል ወታደራዊ ሃይል የተውጣጡ ከ50 ሺህ በላይ የቀድሞ ታጋዮች እንዲነሱ ተደርጓል።

በሐምሌ ወር 2015 ጀምሮ በትካሄደው የመጀመሪያ ምዕራፍ የቀድሞ ታጋዮችን ከሰራዊት የማሰናበት ተልዕኮ በተመለከተ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ጄኔራል ታደሰ ወረደ ሂደቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ብቻ የሚመራ መሆኑን መግለፃቸው ይታወሳል።

“ከመቶ ሺህ በላይ የቀድሞ ታጣቂዎችን  ማሰናበትና ለመልሶ ማቋቋም እና ለመዋሃድ የሚሆን በቂ በጀትና አቅም በሌለበት  የፕሪቶሪያ ስምምነት በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን    ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።  ሲል የጊዜያዊ እስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ መናገሩ አይዘነጋም።   

የብሔራዊ የተሃድሶ ኮምሽን በዲሴምበር 2022 የተቋቋመው በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ውስጥ በተገለጹት ውሎች መሰረት ነው፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን የማፍረስ እና የማገገሚያ ቀዳሚ ሀላፊነት ነው።

እስካሁን ኮሚሽኑ ከስምንት ክልሎች የተውጣጡ 371,971 የቀድሞ ታጣቂዎችን መዝግቧል። እነዚህን ወገኖች ወደ ሰላማዊ ኑሮ ለምመለስ እየተሰራ መሆኑን ኮማሽነር ተሾመ ቶጋ ገልጸው ነበር።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በሁለት ደረጃዎች አካሄድኩት ያለውን ከ100,000 በላይ ተዋጊዎችን ማሰናበቱን በሚመለከት እስካሁን ከሌላ ገለልተኛ ወገን የተሰጠ ምንም አይነት ማረጋገጫ አልተገኘም። en

LEAVE A REPLY