ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ‹‹በጦር ወንጀልና ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የተሳተፉ›› የኤርትራ ወታደሮች ጉዳይ በሌሉበትም ቢሆን፣ በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ በሚቋቋመው ልዩ ፍርድ ቤት ሊታይና ተጠያቂነታቸውም ሊረጋገጥ ይገባል ሲሉ ሰባት የመብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ጥያቄ አቀረቡ፡፡
የሰብዓዊ መብትና የሲቪክ ድርጅቶቹ የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በዝግጅት ላይ ያለውን ረቂቅ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ በተመለከተ ባወጡት መግለጫ፣ ይቋቋማል ተብሎ በሚጠበቀው እውነት አፈላላጊ ኮሚሽን አማካይነት፣ በውጭ ኃይሎች የተፈጸሙ ከባድ ወንጀሎች ይፋ ሊደረጉ፣ እውነቱ ሊታወቅና ሊሰነድ ይገባል ብለዋል፡፡