አሜሪካ በኢትዮጵያ የክልል ጉዳዮች ወደ ግጭት ሊያመራ ይችላል’ ስትል አስጠነቀቀች 

አሜሪካ በኢትዮጵያ የክልል ጉዳዮች ወደ ግጭት ሊያመራ ይችላል’ ስትል አስጠነቀቀች 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የ2024 የአሜሪካ የስለላ ተቋም አመታዊ ግምገማ በፕሪቶሪያ  ስምምነት መሰረት   ያልተፈቱ የክልል ጉዳዮች ወደ ግጭት ሊያመሩ ይችላል” ሲል አስጠንቅቋል።

የአመታዊ ግምገማ ሪፖርቱ የወጣው በአዲስ አበባ በአፍሪካ ህብረት ስብስቢነት ሲካሄድ የነበረው በፌዴራል መንግስቱ እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተካፈሉበት ስብሰባ ማጠቃለያ ላይ ነው።

የአፍሪካ ህብረት ባዉጣው መግለጫ ሁለቱ ወገኖች “በትግራይ ክልል ሰላም፣ ደህንነት እና መረጋጋትን ለማስፈን ሁለገብ ምክክር ለማድረግ” እና “በቋሚነት ለመምከር” ተስማምተዋል። ብሏል

ይህው የአፍሪካ ህብረት መግለጫ በዋናነት በፌዴራል መንግስት እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ የተደረጉ መሻሻሎች እንዳሉ ሲገልጽ  ዝርዝር ጉዳዬችን ከመግለፅ ተቆጥቧል።  

አሁንም ያልተፈታው የምእራብ እና የደቡብ ትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች ከመንግስት ጋር ግንኙነት ባላቸው የአማራ ክልል ሃይሎች ተይዘው የሚገኙበት ሁኔታ፣ የኤርትራ ጦር ከሰሜን ምስራቅ የትግራይ አካባቢዎች መውጣቱ እና የተፈናቃዮቹ ወደ ቀድሞ ቀያቸው በመመለስ ዙሪያ ብዙ ያልተከናወኑ ተግባራት የሰላም ስምምነቱ ሙሉ ለሙሉ ተፈፃሚ እንዳይሆን ያዘገዩት መሆኑን መገለፁ ይታውቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው የአሜሪካን መንግስት የ2024 የግጭት ስጋት ግምገማ አመታዊ የግምገማ ሪፖርት “በህዳር 2022 የጦርነት ማቆም ስምምነት በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራይ ተዋጊዎች መካከል የሁለት አመት ጦርነት ሲያበቃ፣ ያልተፈቱ የክልል ጉዳዮች እንደገና ወደ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ” ሲል ያሳወቀው። en

LEAVE A REPLY