ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በብዙ መስዋዕትነት ከግጭትና ከሰላም ቀውስ ወጥቶ ሰላምና መረጋጋትን ማስፈን ችሏል፡፡ የክልሉ ሕዝብ የተገኘዉን ሰላም ተጠቅሞ ወደ ልማትና የተረጋጋ ሕይወት እየገባ እንደሆነ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ይገነዘባል፡፡
የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በክልሉ ዋና ዋና ከተሞች በዜጎች ላይ ዘግናኝ የሆኑ የግድያ ወንጀሎች በተደጋጋሚ እየተፈጸሙ መሆናቸዉን ለፓርቲያችን የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በግልገል በለስ ከተማ ሁለት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ዉስጥ አንድ የፖሊስ ከፍተኛ መኮንን፣ አንድ ወጣት የኮሌጅ ተማሪ፣ በፓዌ ከተማ አንድ ከፍተኛ ጠበቃና የህግ አማካሪ በጥይት ተመተዉ ተገድለዋል፡፡ በወምበራ ወረዳ አንድ ባለሀብት በግፍ መገደሉም ይታወሳል፡፡
የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በአሶሳ ከተማ አቅራቢያ በሲስተር ትዕግስት ጥላሁን ላይ የተፈጸመዉ ዘግናኝ ጠለፋና የግድያ የወንጀል ድርጊት ፓርቲያችንን ያሳዘነ ሲሆን ተጠርጣርዎች እስከ ዛሬ ድረስ በቁጥጥር ስር አለማዋለቸዉ የዜጎች በሕይወት የመኖር ዋስትና አደጋ ላይ መሆኑን ድርጅታችን ይገነዘባል፡፡
ፓርቲያችን ከተለያየ አቅጣጫ እንደደረሱት መረጃዎች ከሆነ ሲስተር ትዕግስት ጥላሁን ተጠልፋ ከተሰወረችበት የካቲት 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ በግፍ ተገድላ ወንዝ ዳር ተጥላ እስከተገኘችበት የካቲት 27/2016 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ፖሊስ ተገብዉን ክትትል ቢያደርግ በሕይወት ማትረፍ የሚቻልበት ዕድል እንደነበረ እናምናለን፡፡
ባለፉትስድስት ወራት በከተሞች የቡድን ዝርፊያ፣ ውንብድና፣ ሰዎችን መሰወር፣ ህጻናት ማገትና አሰቃቂ ግድያዎች እየተበራከቱ ይገኛሉ። አጥፊዎች ለህግ ቀርበው አስተማሪ ቅጣት ሲጣልባቸው አንመለከትም። ይህ ደግሞ በህብረተሰቡ ውስጥ ስጋትና ጥርጣሬ ከመፍጠሩም በላይ በፍትህ ተቋማት ላይ አመኔታ ማጣት እያመጣ እንደሆነ እንገነዘባለን።
ስለሆነም ፓርቲያችን የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በክልሉ እየተፈጸሙ የሚገኙ የግድያ ወንጀሎችን በተመለከተ የሚከተለዉን ባለ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫ አዉጣቶል
የየአቋም መግለጫው 1. በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የዜጎችን ሕይወት እየነጠቁ ያሉ ወንጀለኞች ታድነዉ ለሕግ እንድቀርቡ፤ በሕግ ቁጥጥር ስር የዋሉት ደግሞ ተገቢዉን ፍርድ እንዲያገኙ ፓርቲያችን የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ይጠይቃል፤
2. የክልሉ መንግስት በክልሉ ድህረ ግጭት ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት እየተለመደ የመጣዉን የግድያ ወንጀል ምክንያት በሚገባ እንዲጠና በማድረግና የወንጀል መከላከል ስራ በመስራት ዜጎች በሰላም ገብቶ መዉጣት እንዲችሉ ተገቢዉን ትኩረት እንዲሰጥ ፓርቲያችን የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ያሳስባል፤
3. በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ለሠላም እጅ ያልሰጡ የታጠቁ ኃይሎች ፀብ ጫሪ እንቅስቃሴ አከባቢውን መልሶ ለግጭት የሚጋብዝ በመሆኑ የፀጥታ ኃይሉ ተገቢውን ጥንቃቄ እና እርምጃ እንዲወሰድ እንዲሁም በከማሽ ዞን ሰዳል ወረዳ መነሻቸውን ከሱዳን ያደረጉ በሰላማዊ ዜጎች እና አንድ የፀጥታ አባል ላይ ያደረሱት ግዲያ እና አካል ጉዳት አከባቢው ላይ የፀጥታ ስጋት የደቀነ በመሆኑ መንግስት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ፓርቲያችን የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ያሳስባል፣
4. በቅርቡ በሲስተር ትዕግስት ጥላሁን ላይ የተፈጸመዉ ዘግናኝ ወንጀል በሴቶች ሰብዓዊ መብት ላይ የተፈጸመ ከፍተኛ ጥቃት መሆኑ ታዉቆ የክልሉ መንግስት ተገብዉን ትኩረት በመስጠት ተጠርጣሪዎች ለሕግ እንዲቀርቡ እንድያደርግ ፓርቲያችን የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በጥብቅ ያሳስባል።ሲል ፓርቲው መግለጫ እሳስቦል ።en