ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ቶም ፔሪሎ ጋር ተወያይተዋል በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች እንዲሁም በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የመከሩ ሲሆንበውይይቱ ላይ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ኢትዮጵያ በሱዳን ሰላም እንዲሰፍን ኢትዮጵያ ስታደርግ የነበረውን ጥረት ገልጸዋል።
ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች ችግሮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በንግግር እንዲፈቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተደረጉ በጎ ጥረቶችን ለልዩ መልዕክተኛው አስታውሰዋል።
ቶም ፔሪሎ በበኩላቸው÷በሱዳን ሰላም እንዲመጣ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተደረገውን ጥረት አድንቀዋል። ሲልሁለቱ አካላት በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አስታውቆል።en