ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአማራ ክልል የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ጋር ተዳምሮ የኑሮ ውድነቱ ሕዝቡን ችግር እያባባሰው መኾኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለአማራ ክልል አመራሮች የጋራ ምክክር ላይ ተናገሩ።
በአማራ ክልል የተፈጠረው የፀጥታ ችግር በሁሉም አካባቢዎች ተገኝተው ሕዝቡን ለማወያየት ቢቸገሩም የምክር ቤት አባላቱ በተለያዩ ዘዴዎች ከሕዝብ የተሰበሰቡ ጥያቄዎችን ለክልሉ ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ አቅርበው በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ እንዲቀየር ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያካተተ ውይይት ሊደረግ ይገባል። ማለታቸው ተሰምቷል። en