ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ለሥራ ማስኬጅያ ከመንግሥት የተሰጠውን 2.7 ሚሊዮን ብር ከታለመለት ዓላማ ውጪ አዉሏል፣ ለመሪዎቹና ለሌሎች አባላቱ የግል ጥቅም ከፍተኛ ገንዘብ አዉጥቷል መዝበራ ተፈፅሞል ሲል የወንጀል ምርመራ እንዲደረግበት ጠየቀ።
ሥለቀረበበት ክስ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጽሑፍ መልስ ማስገባታቸውን ምላሽ የስጡት የአንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ሲሳይ ደጉ “ገቢና ወጪያችን ግልጽ በሆነ በሒሳብ አያያዝ የመጣ ፓርቲ ነው” ሲል የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አድርጓል።
በፖርቲው አመራሮች ተፈጽሟል የተባለው ወንጀል ተጣርቶ እስከሚታወቅ ድረስም ፓርቲውና መሪዎቹ እንዲታገዱ መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። en