ፕሬዚዳንት ፑቲን አሽነፉ

ፕሬዚዳንት ፑቲን አሽነፉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ፑቲን 87 በመቶ ድምጽ በማግኘት የሩሲያን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸውን ተከትሎ በምርጫው ተሳትፎ የነበራቸውን ሩሲውያንን አመስግነዋል፡፡

ሩሲያ ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስከበር የራሷን አማራጭ ትወስዳለች ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጸዋል። ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው  ነፃ፣ ጠንካራና ሉዓለዊት ሩሲያን የመፍጠር ህልማቸው እውን እንዲሆን ከመላው የሩሲያ ሕዝብ ጋር በትብብር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡ 

ሩሲያ በአንድ እጇ የጦር መሳሪያ በሌላኛው እጇ ደግሞ ሕዝቦቿን በማስተባበር አሁን ባለው የነባራዊ ሁኔታ የገጠማትን ችግር ተጋፍጣ ብሄራዊ ጥቅሟን ታስጠብቃለች ነው ያሉት፡፡ 

ከፊታችን ብዙ ሥራዎች ይጠብቁናል ያሉት ፕሬዚዳንቱ÷”አንድ ስንሆን ጠላቶቻችንን አሸንፈናል፣ ለወደፊትም አንድ ሆነን እናሸንፋለን” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከቀድሞ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ስታሊን በመቀጠል ሀገሪቱን ለረጅም ጊዜ መምራት የቻሉት ፑቲን የሀገሪቱ ምርጫ ቦርድ ውጤቱን ይፋ ካደረገ በኋላ ለ5ኛ ጊዜ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚሾሙ አር ቲ ዘግቧል፡፡ en

LEAVE A REPLY