ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ አርብ መጋቢት ፯ቀን፪ሺ፩፮ በሱዳን የተከሰተው አስከፊ ረሀብ እልቂት እንዳያስከትል አስጠንቅቋል።
የእርስ በርስ ጦርነቱ ረሃብን እያባባሰ በመምጣቱ በአስቸኳይ የዕለት ደራሽ እርዳታ ለረሐብተኛው ለማድረስ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ዩኒሴፍ ጠይቋል።
የሱዳን ፓራሚሊታሪ ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች ከሱዳን ጦር ኃይል ጋር ባካሄደው ወራትን ባስቆጠረ ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ተገድለዋል፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ከሀገሪቱ ውስጥ እና ከሀገር ውጭ እንዲሰደዱ እና ለከፋ ረሃብ እንዲዳረጉ ማድረጉን አሁንም ሀገሪቱን ለመቆጣጠር ሁለቱ ኃይሎች እየተፋለሙ መሆናቸውን ዩኒሴፍ አስታውቋል።
አስከፊ እልቂት ለማስቆም ያለውን ዕድል ሲያልፈን በዝምታ እየተመለከትን ነው። ብለዋል የሱዳን ዩኒሴፍ የመስክ ኦፕሬሽን እና ድንገተኛ አደጋ ዋና ኃላፊ ጂል ላውለር በጄኔቭ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተካሄደ ስብሰባ ላይ።
በሱዳን ሠራዊቱ እና በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል በኤፕሪል 2023 ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ዋና ከተማዋ ካርቱም የመጀመርያው የተባበሩት መንግስታት ተልእኮ አካል በመሆን ወደሱዳን አምርታ የነበረችው የሱዳን ዩኒሴፍ የመስክ ኦፕሬሽን እና ድንገተኛ አደጋ ዋና ኃላፊ ጂል ላውለር በጄኔቫ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተካሄደ ስብስባ ላይ ስለ ሱዳን የተከሰተው ሰበአዊ ቀውስ አጭር መግለጫ ሰጥታለች።
በሱዳን በረሃብ የሚሞቱ ሰዎች ህይወት ለመታደግ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የተደረገው ጥረት አልተሳካም። “ረሃብ ተስፋፍቷል – ሰዎች በረሃብ ሳብያ እያለቁ ነው ከሞቾቹ ውስጥ የህፃናትና የእናቶች ሞት የመጀመሪያው ደረጃ ይዞል ” ብለዋል ላውለር። በሌላ በኩል በጦርነቱ የተነሳ የህክምና ተቋማት ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል ለማለት ይቻላል። በዚህ አመት በሱዳን እስከ 3.7 ሚሊዮን የሚደርሱ ህጻናት ከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንደተጋለጡና ቁጥራቸው 730,000 አስቸኳይ የህይወት አድን ህክምና የሚያስፈልጋቸውን መሆኑን ዩኒሴፍ አስታውቋል ። የአለምአቀፉ መኃበረሰብ በሱዳን የተከሰተውን ቀውስ በዝምታ ሊያይ አይገባም ሲል ዩኒሴፍ የሚመለከታቸው አካላትን ወቅታዊና አፋጣኝ ምላሽ ይሰጡ ዘንድ አስጠንቅቋል። || EN-ኢትዬጵያ ነገ ||