በአማራ ክልል የደህንነት ካሜራዎች ሊገጠሙ ነው!! 

በአማራ ክልል የደህንነት ካሜራዎች ሊገጠሙ ነው!! 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለአማራ ክልል 25 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ዘመናዊ የደህንነት ካሜራዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡  እነዚህ ከሜራዎች በቅርቡ ይገጠማሉ ተብሎል።  

ካሜራዎቹን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና በአማራ ክልል የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የከተሞች መሠረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ  ለሆኑት ዶክተር አሕመዲን መሐመድ አስረክበዋል በስነስርአቱ ላይ የደህንነት ካሜራዎች ገጠማ በቅርቡ ይጀመራል ተብሏል ፡፡

ተቋሙ ከተሞችን ስማርት ሲቲ ለማድረግ ሥራ መጀመሩን ጠቁመው÷ ይህን ተግባር ወደ አማራ ክልል በማስፋት ከተሞችን ተጠቃሚ ለማድረግ በትብብር እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ || EN – ኢትዮጵያ ነገ ||

LEAVE A REPLY