በአማራ ክልል የነዳጅ እጥረት ተከስቷል   

በአማራ ክልል የነዳጅ እጥረት ተከስቷል   

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአማራ ክልል ያሉ አሽከርካሪዎች ለከፍተኛ የነዳጅ እጥረት በመጋለጣቸው ሥራቸውን ማከናወን እንዳልቻሉ ተናገሩ።

በክልሉከ280 በላይ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች እንደሚገኙ 253ቱ በሥራ ላይ እንደሚገኙ 27ነዳጅ ማደያዎች አገልግሎት እየስጡ እንዳልሆነ ከክልሉ የተገኝ መረጃ ያስረዳል።

አሽከርካሪዎቹ ለቀናት ሰልፍ በመያዝ ከማደያዎች ነዳጅ ለመቅዳት የሚያደርጉት ጥረትም ውጤት እንደሌለው በምሬት የሚናገሩት አሽከርካሪዎች   የነዳጅ ግብይቱን ጥቁር ገበያው ተቆጣጥሮታል ቤንዚን እስከ 300 ብር  እየተሽጠ ነው ይላሉ ። የአማራ ክልል  በበኩሉ ለነዳጅ አቅርቦት ሦስት መሰረታዊ ችግሮች እንዳጋጠሙት አመልክቷል ። ሆኖም አቅርቦቱን ለማስተካከልና ሕገወጥነትን ለመከላከል ሥራዎች ተጀምረዋልም ብሏል ።(EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY