በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት በሰሜን ጎጃም፣ በደቡብ ጎንደር፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞኖች እና በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማሩ 110 ባለሀብቶች ንብረት ላይ ውድመት ደርሶባቸዋል ነው ያሉት የክልሉ ግብርና ቢሮ ኀላፊ፡፡
በአትክልት፣ ፍራፍሬ እና ቡና ልማት ዘርፍ ለመሰማራት በክልሉ ኢንቨስትመንት በአዲስ ውል የወሰዱ 49 ባለሀብቶች ወደ ልማት አለመግባታቸውንም የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ተናግረዋል ።
በተፈጠረው ችግር ምክንያት ብድር ለመበደር፣ ውል ለማራዘም እና ለማደስ፣ ፕሮጀክት ለመቀየር፣ ከልማት አፈጻጸም ጋር የሚያያዙ ጉዳዮችን ለመፈጸም በባለሀብቶች ላይ ከፍተኛ የኾነ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን አንስተዋል።
ባለሀብቶች በገቢያ ትስስር ችግር ምክንያት ምርታቸውን ከቦታ ቦታ አዘዋውረው ለመሸጥ አልቻሉም፤ ይህም በክልሉ እና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ብለዋል። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)