75 በመቶ የፆታ ጥቃት በኤርትራ ሐይሎች  እንዴት ተፈጽሟል – ፕሬዚዳንት  ጌታቸው ረዳ

75 በመቶ የፆታ ጥቃት በኤርትራ ሐይሎች  እንዴት ተፈጽሟል – ፕሬዚዳንት  ጌታቸው ረዳ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በጦርነቱ ወቅት ለተፈፀሙት ወንጀሎች በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ተጠያቂነት ለማረጋገጥ እየሠራሁ ነው የሚለው የኢትዮጵያ መንግስት ከትግራይ በኩል ተቃውሞ ደርሶበታል።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ ከወራት በፊት ለኢትዮጵያ ፍትሕ ሚኒስቴር በፃፉት ደብዳቤ የሽግግር ፍትሕ ፓሊሲውን መተቸታቸው ይታወሳል። 

በፌደራሉ መንግስት የተቀረፀው የሽግግር ፍትሕ ፓሊሲ የፕሪቶርያውን ስምምነት መሰረት ያላደረገ፣ የትግራይን ልዩ ሁኔታ ያላገናዘበ፣ የትግራይን ወሳኝ ተሳትፎም ያላካተተ ነው ማለታቸው ይታወሳል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ   የትግራይ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንትአቶ ጌታቸው ረዳ፦ «…የሽግግር ፍትሕ ተጠያቂነት ይረጋግጣል ብለን የምናስብ ከሆነ፥  ባሉን መረጃዎቻች መሰረት 75 በመቶ የሚሆን የፆታ ጥቃት የፈፀሙ የኤርትራ ሐይሎች ላይ እንዴት ተጠያቂነት ማረጋገጥ ይቻላል ?»  ብለዋል።  ከተባበሩ መንግስት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮምሽን ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይትን   የተከታተሉ በሰጡት አስተያየት የፌዴራል መንግስቱ ምላሽ  ሲታወቅ  በጉዳዩ ላይ ሰፊ የሆነ ግብረ መልስ ሊገኝ ይችላል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY