ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መጋቢት 11፣ 2016 በአስራሶስተኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች በ3 ሺህ ሜትር የሴቶች የመሰናክል ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌት ሎሚ ሙለታ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡
አትሌቷ 9 ደቂቃ 26 ሰከንድ ከ63 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው 3ኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው፡፡
እንዲሁም አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ እና ፍሬሕይወት ገሰሰ 4ኛ እና 5ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል፡፡
ይህን ውድድር ኬንያዊቷ ቢያትሪስ ቼፕኮዪች 9 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ ከ61 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ክብረወሰን በማስመዝገብ ጭምር ስታሸንፍ÷ ኡጋንዳዊቷ ፔሩዝ ቼሙታይ ሁለተኛ ሆናለች፡፡(enኢትዮጵያ ነገ)