ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሶማሊያ አቅራቢያ የቱርክ ድሮን ጥቃት መፈፀሙንከ 22 በላይ ሰዎችን ሲሞቱ 21 ቆስለዋል ፣ ብዙ ህጻናትን በጥቃቱ መጎዳታቸው ተሰማ።
በዚሁ የመጀመሪያው የድሮን ጥቃት ጉዳት የደረስባቸውን ሰዎች ለማዳን አደጋው ወደደረሰበት ቦታው ሲያመሩ የነበሩ ስዎች ላይ ሁለተኛው የድሮን ጥቃት ተፈፀመ ያሉት የአይን እማኞች ለዋሽንግተን ፖስት እንደተናገሩት ነገሩ እልቂት ነበር” ከተጎዱት መካከል 15 ያህሉ ህጻናት እንደሚገኙበት እና በርካታ ሴቶችም ይገኙበታል ብለዋል።
የቆሰሉት በሞቃዲሾ በሚገኘው መዲና ሆስፒታል ህክምና በማግኘት ላይ ናቸው ብለዋል። በመዲና ሆስፒታል ያሉ ዶክተሮች አስተያየት ለመስጠት ወዲያውኑ አልተገኙም። ( EN ኢትዮጵያ ነገ)