በጎጃም የተለያዩ ከተሞች አሰሳና እስር  እየተካሄደ ነው 

በጎጃም የተለያዩ ከተሞች አሰሳና እስር  እየተካሄደ ነው 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ  በሰሜን ጎጃም በጎንጅ ቆለላ ዙሪያ፣ በገርጨጭ  በዓግታ፣ በመርዓዊ፤ በቲሊሊ  በዜጋንሳ ቀበሌ የመከላከያ ሰራዊት  ለቀናት የዘለቀ አሰሳና እስር እያካሄደ መሆኑን  የአይን እማኞች ተናገሩ። 

መከላከያ ሠራዊት አባላት ክልሉ የፀጥታ ኀይል ጋር በመቀናጀት የፋኖን ትደግፋላችሁ ተብለው የተጠረጠሩ በርካታ ነዋሪዎችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። 

የአይን እማኞች እንደተናገሩት፣  በአካባቢው እየተካሄደ ባለው እሰሳ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ እንደነበረ ነው የተናገሩት። ድርጊቱ በርካታ ወጣቶች ወደ በረሃ እንዲገቡ ማድረጉን እማኞች ተናግረዋል። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY