የአይ ኤምኤፍ ልዑካን በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረገ ነው

የአይ ኤምኤፍ ልዑካን በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረገ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአለም የገንዝብ ድርጅት ከፍተኛ ባለሙያዎች ቡድን በአዲስ አበባ በሚኖረው ቆይታ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ፕሮግራም በማጥናት ለኢትዮጵያ መንግስት የፖሊሲ ለውጥ እንዲያደርግ ጥያቄ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። 

የኢትዮጵያ መንግስት በውጭ በምንዛሪ እጥረት እና በከፍተኛ የዋጋ ንረት የተጎዳውን ኢኮኖሚ ለማረጋጋት 3.5 ቢሊዮን ዶላር ከአይኤምኤፍ ጠየቃለች የሚል ያልተረጋገጠ መርጃ በስፋት እየተዘዋወረ ነው።

አይኤምኤፍ  ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ በሚኖረው ቆይታ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ፕሮግራም በማጥናት የአበዳሪውን ሀሳብ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

ተንታኞች እንደሚሉት ከፖለቲካ መረጋጋት እና ከዕዳው ሁኔታ ስጋት በተጨማሪ አይኤምኤፍ ኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘብ ዲቫልዩት እንድታደርግ   እና የባንክ እና የቴሌኮም ሴክተሮችን ለውጭ ኩባንያዎች እና ባንኮች  ክፍት እንድታደርግ ግፊት እንደሚያደርግ አንዳንድ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ይናገራሉ። (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY