ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአፍሪካ ህብረት ተወካይ እድርጎ የመደበው የ38 ዓመቱ ሚካሂል ኢሊያሼንኮ በዩክሬን የውጭ የስለላ አገልግሎት መኮንን መሆኑ እያነጋገረ ነው።
ዩክሬናዊው ጦር ኃይል የሻለቃ ማዕረግ ያለው ሚካሂል አሊያሼንኮ የውጭ መረጃ የስለላ አገልግሎት አማካሪ ኤክስፐርት ሆኖ ሲስራ ነበር። ከዚያም ከአፍሪካ ህብረት በዩክሬን ልዩ ተወካይ ሆኖ ተመድቧል።
ይህ የፕሬዚዳንት ቭላድሚር ዜለንስኪ ውሳኔ እንግዳ ቢሆንም ኢትዮጵያ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት የስለላ መኩንኑን መመደብ የዩክሬን በአህጉሪቱ ጥቅሞቿን ለማስከበር በቅርበት ለመስራት ያለው ፍላጎት ከፍተኛ እንደሆነ አመልካች ነው ተብሏል። (EN ኢትዮጵያ ነገ)