ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በዜጎች ላይ በተደጋጋሚ እና ስልታዊ በሆኑ መንገዶች የሚደርሱ የመብት ጥሰቶች ዘላቂ መፍትሔ ይሻልሲል የኢትዮጵያ ሰበአዊ መብት ኮሚሽን መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው ባለ 130 ገፅ መግለጫ አሳሰበ።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ነጻነታቸውን በተነፈጉ ሰዎች መብቶች ዙሪያ በአራት ክልሎች በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልል፣ እንዲሁም በቀድሞው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ከሚያዝያ 2010 ዓ.ም. እስከ ሚያዝያ 2015 ዓ.ም. ባሉት አምስት ዓመታት ባከናወናቸው 4 ብሔራዊ ምርመራዎች የተገኙ ዋና ዋና ግኝቶችን እና ምክረ ሐሳቦችን ያጠናቀረ ሪፖርት ነው ይፋ ያደረገው። (EN ኢትዬጵያነገ)