የሸዋሮቢት እና አጎራባች ከተሞች ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት መኖሩ ተገለፀ 

የሸዋሮቢት እና አጎራባች ከተሞች ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት መኖሩ ተገለፀ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋሮቢት ከተማ፣ የቀወት ወረዳ እና አጎራባች አካባቢዎች ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት እንዴለ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ከሸኔ ጋር ግኑኝነት  ያላቸው እና በተደጋጋሚ በአጣዩ ከተማ ፣ ኤፍራታ ግድም ወረዳና ጀዎሃ በተባሉ አካባቢዎች ጥቃት ሲሰነዝሩ  የከረሙ ኃይሎች በሽዋሮቢት ከተማ እና በአጎራባች አካባቢዎች   ኅብረተሰቡ ባልጠበቀበትና ባልተዘጋጀበት ወቅት፣ ወደ ከተማዋ ሰብረው በመግባት ጥቃት ሊሰነዝሩ ይችላሉ ብለው እንደሚሰጉ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

አጣዬ መግባታቸውን የገለፁ የፋኖ ታጋዮች አካባቢውን ሲረብሹና አጣዬን በተደጋጋሚ ሲያቃጥሉ የነበሩ የሸኔንና የመከላከያ ሀይሎችን ደምስሻለሁ ሲሉ በቪድዮ የተደገፈ መግለጫ ሲሰጡ ተስተውለዋል። EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY