ከ3.5 ሚሊዩን በላይ  ተፈናቃዮች እንዳሉ ተገለፀ

ከ3.5 ሚሊዩን በላይ  ተፈናቃዮች እንዳሉ ተገለፀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ 3.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ  እና ቁጥሩ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ተፈናቃዮችን እንዳላካተተ ተገለፀ።

መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም.  የክልል   ተወካዬችና የሰብዓዊ መብት ተሞጋች ድርጅቶች ተወካዬች የተሳተፉበት ስብሰባ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ምክትል ዋና ኮሚሽነር ወ/ሮ ራኬብ መለሰ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስና ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት የሕግና የተቋማት ማዕቀፍ መኖር እንዳለበት ተናግረው፣ የተፈናቃዮችን ፍላጎት ታሳቢ ማድረግም ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ ሲደረግ የመልሶ ማቋቋሚያ ድጋፍ ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ ራኬብ መለስ ‹‹የወደመባቸውን ወይም የተወሰደባቸውን ንብረት፣ መኖሪያ ቤትና መሬት በሙሉ ሊያገኙና ሊካሱ የሚችሉበት ሁኔታ ስለሚያስፈልግ፣ የፍትሕ ሥርዓቱ ትኩረት ሊያደርግበት ይገባል፤›› ሲሉ አሳስበዋል፡፡ (EN – ኢትዮጵያ ነገ)

LEAVE A REPLY