አልታዬ የተባሉ ጸሃፊ በቅርቡ “…ለረጅም አመታተ የጣሉትን ብዕር ድር ካደራበት ሰገባው…” መዝዘው “የተቆለፈበት ቁልፍ” በቃላት ቁልፍተቆላልፏል!” በሚል ርዕስ አስነብበውናል። ዶ/ር በፍቃዱ በቀለ በ“የተቆለፈበት ቁልፍ” መጽሃፍ ላይ በጻፉት ግምገማ ላይ ተነስተውትችታቸውን ያስነበቡን አልታዬ፣ ከስነ-ጽሁፋዊ ትችታቸው በፊት ያስቀደሙት፣ ዶ/ር በፍቃዱ፣ በ‘የተቆለፈበት ቁልፍ’ መፅሐፍ ላይ ያቀረቡት ጽሁፍ “…የወዳጅነት ፍቅር፣ አክብሮትና ስሜታቸውን ነው … ወይስ በእውነት ምክንያታዊ ትችታቸውን?!…” በሚል፣ ምናልባትም “speculation” (ተጨባጭ ማስረጃ የሌለው “ቲዎሪ”) ነው። እንኳንስ አይደለም “ወዳጅ”፤ አባት እና ልጅ ቢሆኑስ አልታዬን ምን አገባዎት?
ልጅ የአባቱን፣ አባት የልጁን ስነ-ጽሁፍ ስራ ቢተች ምን ችግር አለው? ትኩረትዎን ለምን ሃሳቡ እና ጽሁፉ ላይ አላደረጉም?ወዳጅነታቸውንስ መጥቀስ ለምን አስፈለገ? “speculation” ካልሆነ ደግሞ የዶ/ር በቀለን እና የደራሲውን ወዳጅነት አልታዬ ያውቃሉ?ምናልባትም ጽሁፉ ከእውነተኛ ስነ-ጽሁፋዊ ትችት ይልቅ “character assassination”/ሃሳብን ሳይሆን ግለሰብን ማጥቃት (ad hominem) አያስመስልብዎትም?