አቶ ፈቃደ ሸዋቀና በ 62 አመቱ አረፈ

አቶ ፈቃደ ሸዋቀና በ 62 አመቱ አረፈ

/Ethiopia Nage news/:- ቀድሞ የአዲስ አበና ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበሩትና በተለያዩ ድረ ገጾች ላይ በተለይ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጉዳይ ላይ በመጻፍ የሚታወቁት አቶ ፈቃደ ሸዋቀና በአሜሪካን ሃገር ህይወታቸው ማለፉ ታወቀ፡፡

አቶ ፈቃደ በተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ ንግግር በማድረግ ለሃገሩ ያለውን ቅን ምልከታ ያካፍል የነበረ ሲሆን ህወሃት መራሹ መንግስት ስልጣን ከተቆናጠጠ በኋላ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ካባረራቸው 42 መምህራን አንዱ እንደንበርም የሚታወስ ነው፡፡

አቶ ፈቃደ ሸዋቀና በስደት ሃገሩን ከተለየ ከ24 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን ፈገግታና ቅንነቱን በርካቶች ይመሰክራሉ፡፡ አቶ ፈቃደ ግን ከእናት ሃገሩ ሲለይ ፈገግታ በፊቱ ላይ ቢታይም ውስጡ ግን በሃዘን ተሞልቶ እንደነበር ይገልጻል፡፡

በአሜሪካን ሃገር በናሽናል ካንሰር ኢኒስቲቲዩት ውስጥ በሜዲካል ጂኦግራፊ ሪሰርቸር በመሆን ለረጅም ጊዜ ሲያገለግል የቆየው አቶ ፈቃደ ሸዋቀና ባለው ጽኑ የኢትዮጵያዊነት አቋም ምክንያት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተባረው መውጣታቸው ትልቅ ቀውስ መሆኑን ወዳጆቻቸው ግልጸው በአሜሪካ ሃገር አቀፍ ተቋም ውስጥ የመስራት ብቃት ያላቸውን ድንቅ ሰወች የህወሃት መንግስት ማባረሩ ለትምህርት ጥራት ግዴለሽ መሆኑን ማሳያ እንደንበር ገልጸዋል፡፡

ቪኦኤን ጨምር በተለያዩ ራዲዮ ጣቢያዎች ከአፍቃሪ መንግስት ሰዎች ጋር በሚያደርጋቸው ክርክሮች ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በተሞላበት አንደበት ሃሳቡን በመግለጽ የሚመሰከርለት አቶ ፈቃደ ነገሮችን ለሃገር ዘላቂ መፍትሄ የሚመጣበትን መንገድ በመተለም የታወቃል፡፡

አቶ ፈቃደ የሁለት ወንዶችና የአነዲት ሴት ልጅ አባት ሲሆን የልጅ ልጆችም እንዳሉት ታውቋል፡፡

የአቶ ፈቃደ ሸዋቀና የቀብር ስነ ስርአት በመጭው ቅዳሜ በአሜሪካን ሃገር እንደሚፈጸም ተገልጿል፡፡

ለመላ ቤተሰቡና ወዳጅቹ እንዲሁም አድናቂዎቹ ሁሉ መጽናናትን አንመኛለን
/ኢነዝክ/

LEAVE A REPLY