በአውስትራሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ድምጻቸው ለመስጠት ጥቂት ሰዓታት ይቀራቸዋል
/ETHIOPIA Nege News/:- በአለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ሃገራት ድምጻዊያንን በማወዳደርና ለከፍተኛ ሽልማት በማብቃት የሚታወቀው ዘ ቮይስ በአውስትራሊያ የመጨረሻ ተወዳዳሪዎች አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያዊት ወጣት ፋሲካ አያሌው ዛሬ ማታ ውድድሩን በድል እንደምታጠናቅቅ ተገምቷል፡፡
ወጣቷ ፋሲካ ዘ ቮይስ ውድድር ውስጥ ከገባችበት ጊዜ አንስቶ የድንቅዩ ዝነኛ ድምጻዊያንን ሙዚቃዎች አስመስላ በመጫወት በዳኞች ዘንድ በቀላሉ ተቀባይነትን እያገኘችና ለመጨረሻው ቀን ውድድር እንደበቃች የሚታወቅ ቢሆንም በተለይ በአውስትራሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለስኬቷ ሲረባረቡ መሰንበታቸው ከፍተኛ አስተዋጾ ማበርከቱ አይዘነጋም፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚደረጉ ውድድሮች ላይ የተሳተፉና ጥሩ ውጤት ያመጡ ጥቂት ኢትዮጵያዊያን ቢኖሩም ፋሲካ አያሌው ግን እንዲህ አይነት አለም አቀፍ ውድድር ውስጥ በመግባትና ከመጨረሻ ተወዳዳሪወች ውስጥ ለድል የምትጠበቅ በመሆን ብቸኛዋ ሆናለች፡፡
የዚህ አይነት ዝነኛ ውድድር የሚጠናቀቀው ከዳኞች ድጋፍ በተጨማሪ በዋናነት ህዝብ የሚሰጠው የድምጽ ድጋፍ በመሆኑ በአውስትራሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ያላቸውን ጥቂት ሰአታት ተጠቅመው ወጣቷን ድምጻዊት ፋሲካ አያሌውን በመምረጥ ለድል እንድትበቃ አስተዋጽኦዋቸውን ያበረክታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
https://9now.zendesk.com/hc/en-us/articles/115003497168-I-m-outside-of-Australia-Why-can-t-I-watch-9Now-